ሁለት እውነተኛ ታሪኮች፣ ሁለት የግንባታ አለመግባባቶች እና አንድ የተለመደ ስህተት — የጽሑፍ ውል የለም።.
🔹 1ኛ ጉዳይ – አቶ አለሙ እና መንግስቱ ጠ/ተቋራጭ
አቶ አለሙ አሪፍ ቤት ሰርቶ ነሐሴ ላይ ለመግባት አቅዶ ነበር። ነገር ግን በወለልና ግድግዳ ላይ ስንጥቅ በማየቱ፤ መንግስቱ ጠ/ተቋራጭ ኢንዲጠግንለት ይቀጥረዋል የጽሁፍ ውል የለም። አለሙ ለመንግስቱ “ስለ ክፍያ ምንም አትጨነቅ፣ በፍጥነት ስራውን ጨርስ” ይለዋል።
- መንግስቱ ጠ/ተቋራጭ ተጨማሪ ባለሙያዎችን አሳትፎ ቤቱን ጠግኖ ይጨርሳል።
- አለሙ የመጀመሪያዎቹን ሶስት ክፍያዎች ለመንግስቱ ጠ/ተቋራጭ ከፍሏል።
- መጨረሻው ክፍያ ላይ መንግስቱ 20 በመቶ ትርፍ እና 10% ትርፍ ጨምሮ የክፍያ ጥያቄ ላከ።
- አቶ አለሙም “ይህን አልከፍልም!” በማለት ፈቃደኛ አልሆነም።
🔹 2ኛ ጉዳይ – ወ/ት ሰብለ እና ታሜክስ ህ/ተቋራጭ
ወ/ሪት ሰብለ በከፊል የተጠናቀቀ G+5 የንግድ ህንፃ ገዝተው ሁለት ተጨማሪ ወለሎች ወደ ላይ መጨመር ያስባሉ። ታሜክስ ህ/ተቋራጭ በ10 ሚሊየን ብር ስራውን እንዲሰሩ በቃል ይስማማሉ - የጽሁፍ ውል፣ የስራ መጠን፣የጊዜ ገደብ እና መመዘኛ መመሪያዎች የሉም።
- ታሜክስ ህ/ተቋራጭ አንድ ወለል ከጨረሰ በኋላ፣ የ10 ሚሊዮን ክፍያ መጠየቂያ ይልካል።
- ወ/ሪት ሰብለ “ይህ የብር መጠን ለሁለት ወለል እንጂ ለአንድ አይደለም!” ስትል ክፍያውን አልቀበልም ትላለች።
- ወ/ሪት ሰብለ ለመክፈል ፈቃደኛ ስላልሆነች ታሜክስ ህ/ተቋራጭ ሥራውን ያቆማል።
ሁለቱም ጉዳዮች ከባድ ጥያቄዎችን ያስነሳሉ -
-
እነዚህ አለመግባባቶች ወደ ፍርድ ቤት መሄድ አለባቸው ወይንስ ውጭ መፍትሄ ያገኛሉ?
-
ትክክለኛው ማነው - ባለቤት ወይም ኮንትራክተሩ?
-
የቃል ስምምነቶች ሁለቱንም ወገኖች ሊከላከሉ ይችላሉ?
አስተያየትዎን እና ክርክርዎን ለሌሎች አባላት ያካፍሉ።
📢 ብይኑ በ15 ቀናት ውስጥ እዚህ ይፋ ይሆናል። ተከታተሉት!