ደራሲ፥ የግንባታ መፍትሔ ሀሳቦች

  • Why Buildings and Bridges Collapse: Top 10 Reasons You Should Know

    ህንጻዎች እና ድልድዮች ለምን ይፈርሳሉ፡ ማወቅ ያለብዎት 10 ዋና ዋና ምክንያቶች

    አንድ ሕንፃ ወይም ድልድይ የተለመደው ወጥ እና ማራኪ መልክ እስካለው ድረስ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ዘላቂ እንደሆነ ይሰማናል። እነዚህ መዋቅሮች በኢንዱስትሪ ደረጃዎች መሰረት ካልተነደፉ እና ካልተገነቡ ይህ ግምት የተሳሳተ ሊሆን ይችላል። ታዲያ ሕንፃዎች እና ድልድዮች ለምን ይወድቃሉ? ዋና ዋና አስር ዝርዝሮች እነሆ

    በዚህ ርዕስ ላይ ጠቃሚ መጽሐፍትን ያንብቡ

    በሲቪል ምህንድስና የፈረሱ ግንባታዎች ጥናቶች፡ አወቃቀሮች፣ መሠረቶች እና ጂኦአከባቢ
    በ አሲመማ

    መጽሐፉ 50 የእውነተኛ ምህንድስና ውድቀቶችን ታሪክ ያጠናቅራል፤ እንደ የዲዛይን ጉድለቶች፣ የግንባታ ስህተቶች እና ያልተጠበቁ ሁኔታዎችን ፣ የሰጡትን ትምህርቶች በማጉላት ይተነትናል። መጽሐፉ ፅንሰ-ሀሳብን ከተግባር ጋር በማያያዝ፣ተማሪዎች እና ባለሙያዎች ውድቀቶች እንዴት እንደሚከሰቱ እና በቀጣይ ፕሮጀክቶች ላይ እንዴት መከላከል እንደሚችሉ እንዲረዱ ለማስተማር እንደ የማስተማሪያ መመሪያ ተዘጋጅቷል።

    ተጨማሪ መጽሐፍት

    ህንጻዎች ለምን ይወድቃሉ፡ የግንባታ መዋቅሮች እንዴት ይወድቃሉ
    በ ማቲስ ሌቪ እና ማሪዮ ሳልቫዶሪ

    መጽሐፉ የቆዩ እና የቅርብ ጊዜ ሁነቶች ጥናቶችን በመጠቀም አወቃቀሮችን የሚወድቁባቸውን በርካታ መንገዶች ይዳስሳል። በተፈጥሮ ኃይሎች (የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የንፋስ፣ የመሬት መስጠም)፣ የንድፍ ወይም የግብዓት ጉድለቶች፣ ከመጠን በላይ መጫን፣ መዛል እና የድጋፍ እጦት ውድቀቶችን ይሸፍናል። መጽሐፉ ቴክኒካል ማብራሪያዎችን (በግልጽ ቋንቋ) ከእውነተኛ አደጋዎች ጋር ያዋህዳል—እንደ ድልድይ መውደቅ፣ ያልተሳኩ ግድቦች እና የእግረኛ መንገዶችን መገንባት—እና ምህንድስና፣ ቁጥጥር እና ጥገና የወደፊት፤ አደጋዎችን እንዴት መከላከል እንደሚችሉ ላይ ትምህርቶችን ይሰጣል።

    የንድፍ ችግር አይደለም፦ ውድቀቶችን መረዳት
    በ ሄነሪ ፔትሮስኪ

    መጽሐፉ የኢንጂነሪንግ ውድቀቶች እንዴት እንደሚከሰቱ ይመረምራል-በዲዛይን ስህተቶች ምክንያት ብቻ ሳይሆን ውስብስብ በሆነ የሰው፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ሁኔታዎች ምክንያት ጭምር ነው። የማይረሱ አደጋዎችን ይገመግማል - ከድልድይ መውደቅ እና ከነዳጅ መፍሰስ እስከ መዋቅራዊ ውድቀት - እና ውድቀትን መገመት አለመቻል ወይም አደጋን አምኖ መቀበል ብዙውን ጊዜ ውጤቱን እንደሚያባብስ ያሳያል። በመጨረሻም፣ መፅሃፉ ስለውድቀት መረዳት እና እስከ ለሚከተለው አደጋ ሃላፊነት መውሰዱ አስፈላጊ መሆኑን ይሞግታል፡- ውድቀቶች ወደ አስተማማኝ እና ረቂቅ ዲዛይን የሚመሩ ትምህርቶችን ያስተምራሉ።

    በህንፃ ግንባታ ውስጥ የአወዳደቅ ስልቶች
    በ አሲመማ

    መፅሃፉ ህንፃዎች እንዴት እና ለምን እንደሚወድቁ ፣የተለያዩ ውድቀቶችን ዓይነቶችን ፣መንስኤዎቻቸውን እና እንዴት ሊታወቁ እንደሚችሉ ይመረምራል። ምልክቶችን፣ ቴክኒካዊ መንስኤዎችን እና የእያንዳንዱን ውድቀት አይነት ባህሪያትን የሚያሳዩ ብዙ የጉዳይ ጥናቶችን (የመደርደሪያ-አንግሎች፣ የመስታወት ፍንጣቂዎች፣ የግንብ / የፕላንክ ጉዳዮች፣ የክፈፍ ማሳጠር፣ ወዘተ) ይዟል። እንዲሁም የፎረንሲክ ምርመራዎችን እንዴት ማካሄድ እንደሚቻል-የመስክ ስራ፣ የላብራቶሪ ምርመራ፣ የሪፖርት ጽሁፍ እና የባለሙያዎች ምስክርነት ጭምር - እና በመጨረሻም የተብራራ መዝገብ እና የውድቀት ስልቶችን ያካትታል።

    ስኬትን በውድቀት፡ የንድፍ አይታ (ፓራዶክስ)
    በ ሄነሪ ፔትሮስኪ

    መፅሃፉ ውድቀቶች ፈጠራን እንዴት እንደሚያጎለብቱ ያሳያል፤ የንድፍ ብልሽቶችን - ከድልድይ እስከ ጠፈር መንኮራኩሮች በማጥናት - ድክመቶችን ያሳያል፣ መሻሻሎችን ይመክራል እና በመጨረሻም ምህንድስና ደህንነቱ የተጠበቀ እና የበለጠ ስኬታማ እንዲሆን ያደርገዋል።

    1. መዋቅራዊ ብልሽት

    ህንጻዎች እና ድልድዮች ከሰዎች፣ ከእንስሳት፣ ከተሽከርካሪዎች፣ ከነፋስ እና ከመሳሰሉት የሚመጡ ክብደቶችን ለመሸከም የተነደፉ ናቸው። እነዚህ ክብደቶች መዋቅራዊ አካላትን (እንደ ውለል፣ አግዳሚ/ማገር፣ ምሰሶ፣ ወዘተ) በመጠቀም ወደ መሬት ይተላለፋሉ. መዋቅራዊ ብልሽት የሚከሰተው የእነዚህ አካላት ዲዛይን ወይም ውጥን ከላይ የተጠቀሱትን ክብደቶች መቋቋም በማይችልበት ጊዜ ነው። በነዚህ አካላት ውስጥ ያለ ማንኛውም የንድፍ ወይም የግንባታ ስህተት/ችግር በከፊል ወይም በሙሉ መዋቅራዊ ውድቀትን ያስከትላል።

    ለምሳሌ

    ታኮማ ናሮው ድልድይ (አሜሪካ፣ 1940) ፟- ቅጽል ስም “ጋሎፒንግ ገርቲ”፣ በንድፍ ወቅት ግምት ውስጥ ያልገባ በንፋስ ንዝረት ምክንያት የተፈጠረው መዋቅራዊ ብልሽት በአይሮላስቲክ ፍላተር ምክንያት ወድቋል።

    2. የመሠረት ውድቀት

    ሕንፃዎች እና ድልድዮች መሬት ላይ ይገነባሉ። ይህ መሬት ከእነዚህ ግንባታዎች የሚመጡ ክብደቶችን ለመሸከም የተረጋጋ እና ጠንካራ መሆን አለበት። መሠረት ከሕንፃ/ከድልድይ መዋቅሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን ክብደትን ወደ መሬት የሚያስተላልፍ መዋቅራዊ አካል ነው። ደካማ የግንባታ ቦታ ምርመራዎች፣ መጥፎ ዲዛይን/የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ ያልተረጋጋ መሬት ወይም መስጠም ማለት ህንፃ/ድልድይ መስመጥ ወይም መውደቅ ማለት ነው። የታወቁ የሕንፃ/የድልድይ ውድቀቶች ብዙውን ጊዜ ወደ ደካማ ወይም በቂ ያልሆነ መሠረት ያመላክታሉ።

    ለምሳሌ

    ያዘመመው የፒያሳ ግንብ (ጣሊያን) - አሁንም ቆሞ ያለ ግምብ ቢሆንም ከመሠረቱ በታች ባለው ደካማ እና ያልተረጋጋ አፈር ምክንያት ዘንበል ብሎ ይገኛል። በከፋ ሁኔታ፡ ሁሉም ሕንፃዎች ይሰምጣሉ ወይም ይሰነጠቃሉ።

    3. የግንባታ ቁሳቁስ

    የሕንፃዎች እና የድልድዮች ግንባታዎች ከፍተኛ መጠን ያላቸውን የተለያዩ የቁሳቁስ ዓይነቶችን ይጠቀማሉ። የእነዚህ የቁሳቁስ ዓይነቶች ለምሳሌ እንጨት፣ ብረት፣ አርማታ፣ ድንጋይ፣ ጡቦች, ወዘተ ... የእነዚህ ቁሳቁሶች ጥራት በቀጥታ ከጥንካሬያቸው እና ከመሸከም አቅማቸው ጋር የተያያዘ ነው። ዝቅተኛ ጥራት ያለው ቁሳቁስ ጥቅም ላይ ከዋለ፤ የግንባታው መውደቅ የማይቅር ነው። ይህ ቁሳቁስ እንደ የሕንፃ ወይም የድልድይ መጋጠሚያዎች / ምሰሶዎች ባሉ መዋቅራዊ አካላት ውስጥ ጥቅም ላይ ከዋለ፤ መዋቅራዊ ውድቀቱ አደገኛ ይሆናል። ንድፎች ትክክል ቢሆኑ እንኳን ደካማ ቁሳቁሶችን መጠቀም አፈፃፀሙን ያበላሻል፤ ይህም ወደ መሰንጠቅ፣ መሰባበር ወይም በመጨረሻም ውድቀት ያስከትላል።

    ለምሳሌ

    ራና ፕላዛ (ባንግላዴሽ፣ 2013) - ደረጃውን ያልጠበቀ አርማታ እና ብረት ከህገ-ወጥ የግንባታ ማራዘሚያዎች በተጨማሪ ጥቅም ላይ ውለዋል፣ ይህም ከ1,100 በላይ ሰዎችን ለሞት ዳርጓል።

    4. ክብደት

    የሕንፃዎችን እና ድልድዮችን ዲዛይን በሚሠሩበት ጊዜ የጭነቶች ዓይነት እና መጠን የሚሰላው የኢንዱስትሪ ደረጃዎችን በመጠቀም ነው። ከዚህ ከተሰሉ ጭነቶች ወይም ዓይነቶች ትልቅ ልዩነት ከመጣ በመዋቅር አካላት ላይ ያልተጠበቁ ኃይሎችን ያስከትላል ይህም ወደ አስከፊ ውድቀቶች ሊመራ ይችላል። ወድቀት የሚከሰተው ሕንፃዎች እና ድልድዮች ይተጨናነቀ ጭነት፣ ከመጠን ያለፈ ክብደት ወይም ያልታሰበ አጠቃቀም ምክንያት ከንድፍ ክብደት መጠን በላይ ሲሆኑ ነው።

    ለምሳሌ

    ሀያት ሪጀንሲ የእግር መተላለፊያ (አሜሪካ፣ 1981) - በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በዳንስ ዝግጅት ላይ ተሰብስበው፤ በብቃት ያልተነደፈው መጋጠሚያ ክብደት መቋቋም ስላልቻል የ114 ሰዎችን ሞት መንስኤ ሆኗል።

    5. ዝለት እና መበላት

    ዝለት እና መበላት አንድ ቁሳቁስ የመነሻ ጥራቱን በተደጋጋሚ በመጫን፣ በንዝረት ወይም በሙቀት ልዩነት በአገልግሎት ጊዜ የሚያጣበት ነው። በዚህ ሁኔታ ትክክለኛ ምርመራ እና ጥገና መደረግ አለበት ይህም ካልሆነ ወደ ዘላቂ ውድቀት ያመራል።

    ለምሳሌ

    ሲልቨር ድልድይ ውድቀት (አሜሪካ፣ 1967) - ተንጠልጣይ ድልድዩ በአንድ መጋጠሚያ በብረት ዝለት ምክንያት 46 ሰዎችን ለሞት ዳርጓል።

    6. የግንባታ አሰራር

    የግንባታ አሰራር የሰው ሃይል ክህሎትን፣ የመሳሪያ አጠቃቀምን፣ የአሰራር ሂደቱን እና የደህንነት ደረጃዎችን ያመለክታል። ትክክለኛ ያልሆነ የአርማታ ድብልቅ፣ ደካማ ብየዳዎች፣ የተሳሳቱ ማጠናከሪያዎች፣ በአፈጻጸም ጊዜ አቋራጭ መንገዶች መጠቀም እና የክትትል እጦት የተለመዱ ጉዳዮች ናቸው። በግንባታው ወቅት የሰዎች ስህተት እና ቸልተኝነት በቀጥታ ወደ መዋቅራዊ ድክመት እና የረጅም ጊዜ አደጋዎች ያስከስታል።

    ለምሳሌ

    ሎተስ ሪቨርሳይድ አፓርታማ (ቻይና፣ 2009) - ባለ 13 ፎቅ ህንጻ ተገቢ ባልሆነ ቁፋሮ ወድቋል።

    7. የተፈጥሮ አደጋ

    የመሬት መንቀጥቀጦች፣ እሳተ ገሞራዎች፣ ጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተት፣ ወዘተ የተፈጥሮ አደጋዎች ናቸው። የእነዚህ የተፈጥሮ ክስተት ኃይሎች ለህንፃዎች እና ድልድዮች በጣም ትልቅ ናቸው። ነገር ግን የሕንፃዎች እና ድልድዮች ንድፍ እነዚህን ኃይሎች በተወሰነ ደረጃ ግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ይህ ግምት በአደጋ ጊዜ የማምልጫ ጊዜ በመስጠት እና የነፍስ አድን ስራዎችን ለመስራት ወሳኝ ነው።

    ለምሳሌ

    የኮቤ የመሬት መንቀጥቀጥ (ጃፓን, 1995) - አሮጌ መዋቅሮች ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ እንቅስቃሴን ለመቋቋም ስላልተዘጋጁ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕንፃዎች እና ድልድዮች ወድቀዋል።

    8. የውጭ ኃይሎች

    የአፈር መሸርሸር፣ የመሰረት መሰርሰር፣ በኬሚካል መበላት ወዘተ ህንፃዎችን እና ድልድዮችን የሚያበላሹ ሃይሎች ናቸው። በንድፍ ደረጃ ትክክለኛ ምርመራ እና በአገልግሎት ጊዜ ክትትል፤ በእነዚህ ኃይሎች ምክንያት የሚደርሰውን ጉዳት ያቃልላል።

    ለምሳሌ

    I-35 ዋ ሚሲሲፒ ወንዝ ድልድይ (አሜሪካ፣ 2007) - በከፊል በዲዛይን ጉድለቶች ምክንያት ሌላ ደግሞ በውጫዊ ውጥረቶች ፣ የግንባታ ጭነቶችን ጨምሮ በስራ ሰዓት ጭንቅንቅ ወቅት ወድቋል።

    9. የግንባታ እቅድ

    ደካማ እቅድ - በቂ ያልሆነ የግንባታ ቦታ ዳሰሳዎች እና ጥናቶች፣ ደካማ ሎጅስቲክስ፣ የተጣደፉ መርሃ ግብሮች እና ቅንጅት እጥረት - የልተጠበቁ አደጋዎችን ያመጣል። እቅድ ማውጣት ጊዜን፣ ግብዓቶችን ወይም የተለያዩ ገደቦችን ግምት ውስጥ ማስገባት ካልቻለ የግንባታ ጥራት መጔደልን ያስከትላል። ደካማ እቅድ ማውጣት ወሳኝ ማረጋገጫዎች እና ፍተሻዎች እንዲታላፉ ያደርጋል። ይህም የግንባታውን የመፍረስ እድሎችን ይጨምራል። እነዚህ የማይታዩ ወሳኝ የዕቅድ ችግሮች ከላይ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች ጋር በመቀናጀት ሕንፃዎችን እና ድልድዮችን ይጥላሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ ጽሑፋችንን ያንብቡ- የግንባታ እቅድ አወጣጥ ለባለቤቶች እና የፕሮጀክት ሃላፊዎች.

    ለምሳሌ

    ሳምፑንግ ዲፓርትመንት መደብር (ደቡብ ኮሪያ፣ 1995) - ያልተፈቀደ የንድፍ ለውጦች እና ደካማ እቅድ በታሪክ ውስጥ እጅግ ገዳይ ከሆኑት ህንጻዎች አንዱ ወድቆ ከ500 በላይ ሰዎችን ገድሏል።

    10. የግንባታ አስተዳደር

    በጠንካራ ንድፍ እና እቅድ እንኳን ደካማ አስተዳደር ውድቀትን ያመጣል። የክትትል ማነስ፣ በቡድኖች መካከል ያለው ደካማ ግንኙነት፣ የደህንነት ፕሮቶኮሎችን ችላ ማለት እና ወጪ ቆጣቢ እርምጃዎች የፕሮጀክት ታማኝነትን ያበላሻሉ። ውጤታማ የፕሮጀክት አስተዳደር የጥራት ቁጥጥርን፣ ትክክለኛ ቅደም ተከተል፣ ፍተሻዎችን እና የንድፍ ደረጃዎችን ማክበርን ያረጋግጣል - ይህ ካልሆነ ግን አደጋ የማይቀር ነው።

    ለምሳሌ

    FIU የእግረኞች ድልድይ (አሜሪካ፣ 2018) - ማስጠንቀቂያዎች ችላ ተብለዋል እና ቁጥጥር ደካማ ነበር፤ ይህም ከተግጠመ ከጥቂት ቀናት በኋላ ወድቆ ለስድስት ሰዎች ሞት መንስኤ ሆኗል።

    መደምደሚያ

    እያንዳንዱ የግንባታ እና የድልድይ ውድቀት ታሪክን ይናገራል - የተሰበረ አርማታ እና የተጠማዘዘ ብረት ብቻ ሳይሆን የሰዎች ቁጥጥር ፣ ቸልተኝነት ወይም የዝግጅት እጥረትን የመሰክራል። እነዚህን ምክንያቶች በማጥናት መሐንዲሶች፣ ስራ አስኪያጆች እና ባለድርሻ አካላት ታሪክ እራሱን እንዳይደግም መከላከል ይችላሉ። ጠንካራ ዲዛይን፣ ጥራት ያለው ቁሳቁስ፣ የሰለጠነ አሰራር፣ ትክክለኛ እቅድ ማውጣት እና ጠንካራ አስተዳደር በአንድነት ጊዜን የሚፈትኑ መዋቅር ያላቸውን ግንባታዎች ይፈጥራሉ።

    ከታች ባለው የአስተያየት መስጫ ሳጥን በኩል ሃሳብዎን ያካፍሉ።

    ወይም

  • Exploring Civil Engineering Study Areas: Structural, Geotechnical, Transportation, and More

    የሲቪል ምህንድስና ትምህርት አይነቶችን ማሰስ፡ መዋቅራዊ፣ ጂኦቴክኒክ፣ ትራንስፖርት እና ሌሎችም

    From clean water that we drink everyday; to roads/highway that we travel on; to sweet home house buildings that we dwell, all have the finger prints of civil engineering. Civil engineering as a backbone of civilization through out history. It serves the need of people and communities by designing and building houses, buildings, bridges, railways, tunnels, water treatment plants, pipe lines, and so on.

    civil engineering sub-fields

    ሲቪል ምህንድስና የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ከእቅድ አንስቶ፣ በዲዛይን፣ በግንባታ/ግንባታ፣ ቁጥጥር እና በጥገና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደርጋል። ሲቪል ምህንድስና ቆሻሻን እና ብክለትን ለመቆጣጠር የሚረዱ መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢን እዲኖር ያደርጋል።

    በዚህ ርዕስ ላይ ጠቃሚ መጽሐፍትን ያንብቡ

    የሲቪል ምህንድስና አስደናቂ ገጽታዎች
    በ ኤል ኢ ካርማይክል

    መጽሐፉ የሲቪል መሐንዲሶችን ታሪክ እና ሚና አጉልቶ ያሳያል፣ እንደ ድልድይ፣ ዋሻዎች እና ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ያሉ ታዋቂ ፕሮጀክቶች ያወራል፣ አንባቢዎችን በገሃዱ ዓለም ምሳሌዎች እና የስራ ግንዛቤዎች የሚያስተምር ነው።

    ተጨማሪ መጽሐፍት

    የሲቪል ምህንድስና መስክ አጠቃላይ እይታ
    በ ሼንግ ታኡር ማው

    መፅሃፉ ሙያውን የሚያስተዋውቅ ሲሆን ታሪኩን ፣ ዋና ዋና ቅርንጫፎቹን እና መሐንዲሶች መሰረተ ልማትን በመንደፍ እና በመንከባከብ ረገድ የሚጫወቱትን ወሳኝ ሚና አብራርቷል።

    ሲቪል ምህንድስና፡ በጣም አጭር መግለጫ
    በ ዴቪድ ሙር ውድ

    መጽሐፉ ስለ ሙያው አጭር እይታን ያቀርባል፤ ከታሪኩ ጀምሮ፣ ቁልፍ ሰዎችን እና እንደ ድልድይ፣ ዋሻዎች እና የውሃ ስርዓቶች ያሉ አስፈላጊ ስራዎችን በመዳሰስ የኢነርጂ እና የዘላቂነት ዘመናዊ ተግዳሮቶችን ጭምር ይተነትናል።

    ምህንድስና በግልጽ እይታ - ለተገነባው አካባቢ የመስክ መመሪያ
    በ ግራዲ ሂልሃውስ

    መጽሐፉ ከኤሌክትሪክ መስመሮች እና ድልድዮች፤ እስከ የውሃ ስርዓቶች እና ዋሻዎች፤ በአካባቢያችን ያሉ መሠረተ ልማቶች እንዴት እንደሚሠሩ ያገልጻል። አብዛኛውን ጊዜ ሳይስተዋሉ የሚታለፉ የዕለት ተዕለት የምህንድስና ስራ ውጤቶችን፤ መሐንዲሶች ያልሆኑ ሰዎች የተገነባውን አካባቢ በአዲስ አይኖች “እንዲያዩ” ለመርዳት፣ እንዲያውቁ ለማድረግ በግልጽ ጽሑፍ፣ ስዕላዊ መግለጫዎች እና አጭር ማብራሪያዎችን ተጠቅሟል።

    የከተማ ምህንድስና፡ መሠረተ ልማት እንዴት እንደሚሰራ (ፕሮጀክቶች እና መርሆዎች ለጀማሪዎች)
    በ ማቲስ ሌቪ እና ሪቻርድ ፓንቺክ

    መጽሐፉ እንደ ውኃ፣ ኤሌክትሪክ፣ ጋዝ፣ ፍሳሽ ማስወገጃ፣ ድልድይ፣ መንገድ እና ሽቦ ያሉ የተደበቁ የከተማ ሥርዓቶች እንዴት እንደሚሠሩና አገልግሎት እንደሚሰጡ ያብራራል። እነዚህ መሠረተ ልማቶች በከተማ ዕድገት እንዴት እንደተሻሻሉ ይዳስሳል፤ መርሆችን ለማስተማር ሥዕላዊ መግለጫዎችን፣ ሙከራዎችን እና ጨዋታዎችን ይጠቀማል፤ እና ሁለቱንም የሚታዩ እና የማይታዩ የከተማ ምህንድስና ክፍሎችን ያሳያል

    The Corniche mixed-use development, three landmark towers, London
    የኮርኒሽ ቅይጥ ህንፃ ልማት፣ ሶስቱ ልዩ ማማዎች፣ ለንደን

    መዋቅራዊ ምህንድስና (ስትራክቸራል ምህንድስና)

    መዋቅራዊ ምህንድስና ግንባታውች ላይ የሚያርፉ ወይም የሚመጡ ኃይሎች ካጠና በኋላ እነዚህ ኃይሎች ወደ መሬት እንዴት ያለስጋት እንደሚተላለፉ ይወስናል።

    ለተጨማሪ ማብራሪያ መዋቅራዊ ምህንድስና (ስትራክቸራል ምህንድስና)

    መዋቅራዊ ምህንድስና በአንድ መዋቅር ላይ የሚከሰቱ ኃይሎችን ያጠናል፤ እነዚህ እንዴት መሸከም እና በትክክል ወደ መሬት ማስተላለፍ እንደሚቻል የተለያዩ ስሌቶችን ይሰራል። ኃይሎቹ ከሰው፣ ከእንስሳት፣ ከተሽከርካሪ፣ ከነፋስ፣ ከመሬት መንቀጥቀጥ፣ ከውሃ፣ ወዘተ ሊመጡ ይችላሉ።

    በህንፃ ግንባታዎች ላይ መዋቅራዊ (ስትራክቸራል) መሐንዲስ ከሥነ-ሕንፃ መሐንዲስ ንድፎችን ይቀበላል። ከዚያም ሸክሞችን ለመሸከም እና መሬት ላይ ለመቆም የሚያስችል የሕንፃውን የተለያዩ ክፍሎች (ምሶሶዎች፣ አምዶች፣ ማገሮች፣ ወዘተ) ተንትኖ ይነድፋል። በተጨማሪም መዋቅራዊ (ስትራክቸራል) መሐንዲሶች በድልድዮች፣ ማማዎች እና ሌሎች የሲቪል ምህንድስና መዋቅሮች (ስትራክቸሮች) ላይም በተመሳሳይ ስራዎች ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደርጋሉ። እንደ መዋቅሩ (ስትራክቸሩ) ዓይነት የመዋቅር (ስትራክቸራል) መሐንዲሶችን የሕንፃ፣ የድልድይ፣ ሌላም መዋቅራዊ (ስትራክቸራል) መሐንዲስ ወዘተ ተብለው ይሰየማሉ።

    ጂኦቴክኒካል (የአፈር ምርመራ) ምህንድስና

    ይህ መስክ መሬቱ እንደ ህንፃዎች፣ ድልድዮች እና ግድቦች ያሉ መዋቅሮች በአስተማማኝ ሁኔታ መሸከም እንዲችል የአፈር እና የድንጋይ አለት ጥንካሬ እና ባህሪ ያጠናል።

    Bridge pier supported the ground
    በህንድ ሙምባይ የኬብል ተንጠልጣይ ድልድይ ምሰሶዎች
    ለተጨማሪ ማብራሪያ ጂኦቴክኒካል (የአፈር ምርመራ) ምህንድስና

    ሁሉም በሚባል ደረጃ የሲቪል ምህንድስና መሰረተ ልማቶች በተፈጥሮ እና/ወይም ሰው ሰራሽ መሬት ላይ ይቀመጣሉ/ያርፋሉ። የጂኦቴክኒክ (የአፈር ምርመራ) ምህንድስና የመሬቱን የመሸከም አቅም እና መስጠም ባህሪ ያጠናል። ይህ መስክ በመሬት ውስጥ ያለውን የአፈር እና የድንጋይ ባህሪ እና ጥንካሬ ያጠናል።

    ግዙፍ ግንባታዎች ለምሳሌ፦ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች፣ ድልድዮች፣ ግድቦች፣ ወዘተ ያሉ መዋቅሮች (ስትራክቸሮች) በሚያርፉበት መሬት ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራሉ። ይህ ጫና ወይም ክብደት ግንባታዎቹ ያረፉበት መሬት ውስጥ ውጥረት እና መስጠም ያስከትላል። እነዚህ ውጥረቶች እና የመስጠም አዝማምያዎች ከሚፈቀደው ገደብ በላይ ከሆኑ፤ ህንጻው ወይም ድልድዩ ሊወድቅ ወይም ሊያዘም ይችላል። በተጨማሪም ይህ መስክ ስለመሬት መንሸራተት እና መሬት መንቀጥቀጥ ያጠናል።

    የግንባታ ግብዓቶች (ቁሳቁስ) ምህንድስና

    የግንባታ ግብዓቶች (እቃዎች) ምህንድስና ጥራትን የሚያረጋግጡ መስፈርቶችን በማዘጋጀት፣ በቤተ ሙከራ፣ እና በመስክ ውስጥ የቁሳቁስ ባህሪን በማጥናት ላይ ያተኩራል።

    ለተጨማሪ ማብራሪያ የግንባታ ግብዓቶች (ቁሳቁስ) ምህንድስና

    የግንባታ እቃዎች የሲቪል ምህንድስና መዋቅሮችን (ስትራክቸሮችን) ለመገንባት ወይም ለመስራት የሚያገለግሉ እቃዎች ወይም ነገሮች ተብለው ሊገለጹ ይችላሉ። እንደ ኮንክሪት፣ ድንጋይ፣ እንጨት፣ ብረት፣ አስፋልት፣ አፈር፣ ጡቦች፣ ብሎክይቶች፣ አሉሚኒየም፣ መስታወቶች፣ ፕላስቲኮች፣ ጂኦሲንቲቲክስ፣ ወዘተ የመሳሰሉ ብዙ የግንባታ እቃዎች አሉ። እነዚህ ቁሳቁሶች ሸክሞችን ለመሸከም እና ሌሎች የአካባቢ ሁኔታዎችን ለመቋቋም ልዩ ጥራቶች ሊኖራቸው ይገባል።

    የግንባታ ግብዓቶች (እቃዎች) ምህንድስና የእነዚህን ቁሳቁሶች ባህሪ በመስክ እና በቤተ ሙከራ ላይ ያጠናል። የታቀደውን ጥራት ለመድረስ የተወሰኑ መስፈርቶችን ያበጃል።

    የመጓጓዣ (የትራንስፖርት) እና የትራፊክ ምህንድስና

    የመጓጓዣ (የትራንስፖርት) እና የትራፊክ ምህንድስና ለልማት እና እድገት አስፈላጊ የሆነውን ቀልጣፋ ትራንስፖርት ለማስቻል መሰረተ ልማቶችን ማቀድ፣ መንደፍ፣ መገንባት እና ማስተዳደርን ያካትታል።

    በሞስኮ, ሩሲያ ውስጥ ውስብስብ የሀይዌይ እና የባቡር መስመር ማሳለጫ
    ለተጨማሪ ማብራሪያ የመጓጓዣ (የትራንስፖርት) እና የትራፊክ ምህንድስና

    መጓጓዣ በአጠቃላይ ሰዎችን፣ ሸቀጦችን፣ ቁሳቁሶችን፣ እንስሳትን እና የመሳሰሉትን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ማንቀሳቀስ ወይም መውሰድ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል። ለዚሁ ዓላማ መጓጓዣዎች እንደ ጋሪዎች፣ ተሽከርካሪዎች፣ አውቶቡሶች፣ የጭነት መኪናዎች፣ ባቡሮች፣ አውሮፕላኖች፣ ወዘተ ያስፈልጋል። እነዚህ መጓጓዣዎች የሚጠቀሙበት መንገዶች፣ ድልድዮች፣ የባቡር መስመሮች እና የአየር ማረፊያዎች መሠረተ ልማቶች ያስፈልጋቸዋል።

    የትራንስፖርት እና የትራፊክ ምህንድስና እነዚህን መሠረተ ልማቶች ማቀድ፣ መንደፍ፣ መገንባት/መስራት፣ ማስተዳደር እና መንከባከብ ነው። ማንኛውም ከፍተኛ የእድገት ግብ ያለው ህዝብ ወይም ሀገር ትክክለኛ እና ቀልጣፋ የትራንስፖርት እና የትራፊክ አስተዳደር ስርዓቶችን ሊኖረው ይገባል።

    የግዙፍ ኮንክሪት ስበት (ግራቪቲ) ግድብ፣ ላጋን ዳም፣ ስኮትላንድ ተራራማ አካባቢዎች

    የሃይድሮሊክ ምህንድስና

    የሃይድሮሊክ ምህንድስና ውሃ እንዴት እንደሚንቀሳቀስ እና የእንቅስቃሴውን ባህሪ በማጥናት ላይ ያተኩራል። እና እንደ ግድቦች፣ ቦዮች እና ድልድዮች ያሉ ግንባታዎችን በመንደፍ ውሃ በሚፈለገው ቦታ ለመቆጣጠር፣ ለማከማቸት እና ለማዳረስ ይሰራል።

    ለተጨማሪ ማብራሪያ የሃይድሮሊክ ምህንድስና

    ሁሉም ህይወት ያላቸው ነገሮች ለመኖር ውሃ ይፈልጋሉ። ይሁን እንጂ ውሃ በሁሉም ቦታ አይገኝም። ይህ ማለት ውሃን ከአንድ ቦታ ማጓጓዝ ያስፈልጋል። የሃይድሮሊክ ምህንድስና በመንፈልገው አካባቢ ውስጥ የውሃ እንቅስቃሴን እና ማጠራቀምን ያጠናል።

    የሃይድሮሊክ ኢንጂነሪንግ የውሃ እንቅስቃሴን እንደ ፈሳሽ ኃይል እና ውጤት ይተነትናል። ሃይድሮሊክ ኢንጂነሪንግ ለግድቦች፣ ድልድዮች፣ የመስኖ ቦዮች፣ ድልድዮች ወዘተ ሞዴሎችን በማዘጋጀት ውሃ ተከማችቶ ወደታሰበበት ቦታ ያለ ምንም ችግር እንዲጓጓዝ ያደርጋል።

    የአካባቢ ምህንድስና

    የአካባቢ ምህንድስና የአካባቢን እና የህዝብ ጤናን ልመጠበቅ ይሰራል፤ ውሃን፣ አየርን እና ቆሻሻን ለመቆጣጠር እና ለማስወገድ የሚረዱ ግንባታዎች በመንደፍ፣ በመገንባት እና በማስተዳደር ነው። በዚህ መስክ ውስጥ ያሉ ሲቪል መሐንዲሶች እንደ ንፁህ ውሃ አቅርቦት ፣ የቆሻሻ ውሃ ማጣሪያ ፣ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓቶች ፣ የብክለት ቁጥጥር እና ዘላቂ የግንባታ ልምዶች ባሉ ፕሮጀክቶች ላይ ይሰራሉ።

    ለተጨማሪ ማብራሪያ የአከባቢ ምህንድስና

    ይህ የሲቪል ምህንድስና መስክ የአካባቢን ሀብቶች አጠቃቀም ከሚያጠናው የአካባቢ ሳይንስ ጋር የተዋሀደ ነው። የአካባቢ ምህንድስና ጥናቶችን፣ እቅዶችን፣ ንድፎችን፣ መስሪያ ቦታዎችን ለሚከተሉት ዓላማዎች ይገነባሉ፦

    • ለሰዎች ንጹህ ውሃ ለማቅረብ
    • የቆሻሻ ውሃ አያያዝ
    • የብክለት ቁጥጥር
    • ቆሻሻ መሰብሰብ እና ማስወገድ

    በአጠቃላይ የአካባቢ ምህንድስና ንፁህ የመጠጥ ውሃ እና የምንኖርበት አካባቢ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን የማከሚያ ፋብሪካዎችን በመገንባትና ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዎችን በማዘጋጀት አስተዋጽኦ ያደርጋል።

    የግንባታ አስተዳደር

    የኮንስትራክሽን አስተዳደር ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ፣ በበጀት እና በጥራት እና በደህንነት ደረጃዎች መጠናቀቁን ያረጋግጣል። የግንባታ ፕሮጀክትን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የማቀድ፣ የማስተባበር እና የመቆጣጠር ሂደትን ያካትታል።

    ለተጨማሪ ማብራሪያ ግንባታ አስተዳደር

    ከላይ የተገለጹት አብዛኛዎቹ የሲቪል ምህንድስና መስኮች እርስ በርስ የተያያዙ ሲሆኑ የተወሰኑ መዋቅሮችን (ስትራክቸሮችን) ማቀድ፣ መተንተን፣ መንደፍ እና ሞዴል ማድረግን ያካትታሉ። እነዚህን መዋቅሮች (ስትራክቸሮች) በትክክል ለመገንባት ወይም ለመስራት የግንባታ አስተዳደር ያስፈልጋል። የኮንስትራክሽን አስተዳደር ዕቅዶች፣ ግምቶች፣ ጨረታዎች፣ ግንባታዎች እና ሁሉንም የሲቪል ምህንድስና መዋቅሮችን (ስትራክቸሮችን) መጠገን ያካትታል።

    የግንባታ አስተዳደር የሚጀምረው የአንድን ፕሮጀክት ፍላጎትና መስፈርቶች በማጥናት ነው።

    ክለሳ

    ሲቪል ምህንድስና የዕለት ተዕለት ህይወታችን ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀላል የሚያደርጉ ልዩ ልዩ መዋቅሮችን የሚገነባበት እና/ወይም የሚሰራበት የኑሯችን ወሳኝ አካል ነው። ሲቪል ምህንድስና የሚከተሉትን ያቀርባል፦

    • አስተማማኝ እና ምቹ ቤቶች፣ ሕንፃዎች፣ ቢሮዎች
    • ፈጣን እና ምቹ መንገዶች ፣ ድልድዮች ፣ የባቡር መስመሮች ፣ የአየር ማረፊያዎች
    • የመጠጥ፣ የመታጠቢያ፣ የመዋኛ ውሃ
    • ለጤናማ አካባቢ የቆሻሻ ውሃ አያያዝ
    • የብክለት ቁጥጥር እና ቆሻሻ አያያዝ
    • የተፈጥሮ አደጋዎች ለመቀነስ የሚረዱ መመሪያዎች

    ከላይ ያለውን የአኗኗር ዘይቤ ለመጠበቅ የሲቪል ምህንድስናን በትክክል ማጥናት እና መተግበር አስፈላጊ ነው። ፕሮጄክቶችን ለማካሄድ በእያንዳንዱ ልዩ መስክ ውስጥ ያሉ የሲቪል ምህንድስና ባለሙያዎች መቅጠር እና መጠቀም አስፈላጊ ነው። በሚቀጥለው ጽሑፋችን ከሲቪል ምህንድስና ጋር በተያያዘ የተከሰቱ አደጋዎች እና መንስኤዎቻቸውን እንተነትናለን።

    ከታች ባለው የአስተያየት መስጫ ሳጥን በኩል ሃሳብዎን ያካፍሉ።

    ወይም