ትክክለኛውን የግንባታ ውል መምረጥ፡ ዓይነቶች፣ ደረጃዎች እና ምርጥ ተሞክሮዎች

Project methods available various options

የግንባታ ኮንትራት ፕሮጀክቶችን ለማስተዳደር በጣም አስፈላጊ እና ፕሮጀክቶቹ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቁ ከፍተኛ አስተዋጸ ያበረክታል። ደረጃውን የጠበቀ ኮንትራት ሰነድ ለማዘጋጀት የተለያዩ አይነት ኮንትራቶችን መረዳት ያስፈልጋል። በተጨማሪም የኢንዱስትሪ ደረጃዎች እና ምርጥ ተሞክሮዎች ለእነዚህ ኮንትራቶች ውጤታማነት አስተዋፅኦ ያደርጋሉ።

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የተለያዩ የግንባታ ዓይነቶችን፤ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ደረጃዎች፤ እንዲሁም ለተለያዩ የፕሮጀክት ዓይነቶች የኮንትራት ውል ዓይነት ጥቅሞች/ጉዳቶች እንመለከታለን።

የግንባታ ውል ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?

የግንባታ ኮንትራቶች በአጠቃላይ በአራት መሰረታዊ ምድቦች ሊከፈሉ ይችላል። ምንም እንኳን የተለያዩ መፅሀፎች ይህንን አከፋፈል ወደ ብዙ ምድቦች ቢያበዙትም፤ በእነዚህ አራት ምደቦች ላይ አንድ ተጨማሪ ምድብ እንጨምራለን ።

1 ቁርጥ ወይም ቋሚ ዋጋ ኮንትራት ውል

የቁርጥ ዋጋ ኮንትራቶች የቋሚ ዋጋ ኮንትራቶች በሚባል ስያሜም ይታወቃሉ። በቀላል አነጋገር አንድ ባለቤት እና ሥራ ተቋራጭ በድርድር መጀመሪያ ላይ በፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ ላይ ይስማማሉ። እና ይህ የተስማሙበት ወጪ ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ አይስተካከልም ወይም አይቀየርም። ጠቅለል ያለ ምሳሌ ለመስጠት፡- “አንድ ግለሰብ እና ሥራ ተቋራጭ በ5 ሚሊዮን ብር ወጪ G+2 የመኖሪያ ሕንፃ ለመገንባት ተስማምተዋል።”

ቁርጥ ወይም ቋሚ ዋጋ ኮንትራት ጠቀሜታቁርጥ ወይም ቋሚ ዋጋ ኮንትራት ጉዳት
+ ባለቤቱ የፕሮጀክቱን ጠቅላላ ወጪ ከጅማሬው እንዲያውቅ ይረዳል።
+ ሥራ ተቋራጩ ውጤታማ የግንባታ ዘዴዎችን በመጠቀም ትርፉን ከፍ ማድረግ ይችላል።
- በግልጽ የተቀመጠ የስራ መጠን ላላቸው ፕሮጀክቶች ብቻ ይሰራል።
– ሥራ ተቋራጩን ለኪሳራ ሊዳርግ ይችላል።
– በግንባታ ወቅት የሚመጡ ልውጦችን ማስተናገድ አስቸጋሪ ነው።

2 የነጠላ ዋጋ ኮንትራት ውል

የነጠላ ዋጋ ኮንትራቶች የፕሮጀክት ሥራዎችን እንደ የስራ ሰዓት፣ ሜትር፣ ሊትር፣ ኪሎ ግራም እና የመሳሰሉት መጠን መለኪያዎች ይከፋፍሏቸዋል። በመቀጠልም አንድ ኮንትራክተር ለእያንዳንዱ ነጠላ ሥራ ወይም አቅርቦት ዋጋ ይመድባል። እነዚህን ነጠላ ዋጋዎች በመደመር ጠቅላላ የፕሮጀክቱን ወጪ ግምት ያወጣል። በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀ የንድፍ እና የዋጋ ግምት፤ የፕሮጀክቱን አጠቃላይ ወጪ በግልፅ በማሳየት ባለቤቱንም ሆነ ተቋራጩን ሊጠቅም ይችላል።

ጥቅም፡ የነጠላ ዋጋ ኮንትራት ውልጉዳት፡ የነጠላ ዋጋ ኮንትራት ውል
+ ፕሮጀክቱ እንዲቀል እና በክፍል ክፍል የተከፋፈለ እንዲሆን ይረዳል።
+ ሥራ ተቋራጩ ለእያንዳንዱ ነጠላ ሥራ ወይም አቅርቦት ዋጋ ለማውጣት ሊመቸው ይችላል።
+ በግንባታ ወቅት የሚመጡ ልውጦችን ለማስተናገድ ይቀላል።
– የፕሮጀክቱን ጠቅላላ ወጪን ለማወቅ አስቸጋሪ ነው።
– ሥራ ተቋራጩን የነጠላ ሥራ ወጪዎችን በደንብ ካልገመተ ለኪሳራ ሊያጋልጥ ይችላል።
– ሥራዎች በጥንቃቄ መለካት እና ማረጋገጫ ዘዴዎች መበጀት አለባቸው።

3 የጊዜ እና ግብዓቶች ኮንትራት ውል

በዚህ አይነት ውል ውስጥ ባለቤቱ ከፕሮጀክቱ ጋር የተያያዙ ግብዓቶችን እና ጉልበትን ዋጋ ለመክፈል ቃል ሲገባ፤ የተወሰነ መጠን ያለው ትርፍ ለሥራ ተቋራጩ ይስባል። ይህ ውል የፕሮጀክቱ የሥራ መጠን በትክክል ባልታወቀበት ሁኔታ፤ ፕሮጀክት ግንባታ ለመጀመር ፈጣን ዘዴ ነው።

ጥቅም፡ የጊዜ እና ግብዓቶች ኮንትራት ውልጉዳት፡ የጊዜ እና ግብዓቶች ኮንትራት ውል
+ በሁለቱም የንድፍ እና የግንባታ ሂደቶች ላይ የስራ ላይ ማሻሻዮችን ይደግፋል።
+ ሥራ ተቋራጩ ላይ ሊመጣ የሚችለውን የኪሳራ አደጋ ይቀንሳል ።
+ ፕሮጀክት ግንባታ ለመጀመር ቀላል ነው።
– የዋጋ ጭማሪ ሊከሰት ይችላል።
– የተጠናከረ እና በሚገባ የተደራጀ የፕሮጀክት አስተዳደር ያስፈልገዋል።
– ለአነስተኛ ፕሮጀክቶች ብቻ የሚመከር ነው።

4 ወጪ እና ተጨማሪ ክፍያ ኮንትራት ውል

የግንባታ ፕሮጀክት ባለቤት ከፕሮጀክቱ ሥራ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን ሙሉ በሙሉ በመክፈል [ወጪ] እና ለኮንትራክተሩ የተወሰነ ተጨማሪ መጠን [ተጨማሪ] ለመክፈል ይስማማል። ይህ ውል የፕሮጀክት ሥራ መጠን በግልፅ ካልተቀመጠ ወይም በጊዜ ሂደት የሚቀያየር ከሆነ ሊያገለግል ይችላል።

ጥቅም፡ ወጪ እና ተጨማሪ ክፍያ ኮንትራት ውልጉዳት፡ ወጪ እና ተጨማሪ ክፍያ ኮንትራት ውል
+ ሥራ ተቋራጩ ከኪሳራ አደጋ ይከላከላል።
+ ፕሮጀክቶች ላይ የግንባታ ስልት ፈጠራን ያበረታታል።
– የፕሮጀክት ወጪ መገመት አይቻልም።
– የተጠናከረ እና በሚገባ የተደራጀ የፕሮጀክት አስተዳደር ያስፈልገዋል።

5 የንድፍ-ግንባታ ኮንትራት ውል

ይህ የኮንትራት አይነት የንድፍ እና የግንባታ ሂደቶችን አንድ ላይ ያጣምራል። ይህ ውል በተወሰነ ደረጃ የፕሮጀክት አፈፃፀም፣ ጥረት፣ እና ጊዜ በተመሳሳይ ጊዜ እንዲከናወኑ ያደርጋል። ሥራ ተቋራጩ ለዲዛይን እና ለግንባታ ኃላፊነት ያለው በመሆኑ ፍጥነት እና ውጤታማነት ማምጣት ይችላል።

ጥቅም፡ የንድፍ-ግንባታ ኮንትራት ውልጉዳት፡ የንድፍ-ግንባታ ኮንትራት ውል
+ ውስብስብ ፕሮጀክቶችን ለመስራት ጥሩ ነው።
+ የግንባታ ፍጥነት ያመጣል።
+ ለዲዛይን እና ግንባታ ቡድኖች ትብብር ጥሩ ነው።
– የፕሮጀክት ወጪ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል።
– የንድፍ ማሻሻያዎችን ለማስተናገድ አስቸጋሪ ነው።  

ለእነዚህ የግንባታ ኮንትራት ዓይነቶች አግባብነት ያላቸው መመሪያዎች የትኞቹ ናቸው?

ከላይ የተጠቀሱት የኮንትራት ውል ዓይነቶች ውላቸው ሲያዘጋጅ ግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው የራሳቸው ልዩ ባህሪያት አሏቸው። እነዚህን ልዩ ባህሪያት ለማካተት ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ መመሪያዎች ተዘጋጅተዋል። በብዛት ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ መመሪያዎች የሚከተሉት ናቸው።

  • ፊዲክ (FIDIC) የውል አንቀጾች፦ በአለም አቀፍ ደረጃ እና በአገራችን በብዛት ጥቅም ላይ የሚውለው የኮንትራት አይነት ነው። ይህ ውል ለተለያዩ የግንባታ ኮንትራት ዓይነቶች ሰነድ ለማዘጋጀት ተስማሚ ነው።
  • ሞውድ መመሪያ (MoWUD Standard) የውል አንቀጾች፦ የኢትዮጵያ ሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ይህንን ስምምነት በ1994 ዓ.ም ያረቀቀው ለኮንስትራክሽን ውሎች እንዲውል በማሰብ ሲሆን ለሚፈለገው የኮንትራት ዓይነት ሙያዊ ማሻሻያ ግን ያስፈልገዋል።
  • የፒ.ፒ.ኤ (PPA) ውል፡- የኢትዮጵያ ፌዴራል የመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ ለግንባታ ፕሮጀክት የሚሆኑ የውል አንቀጾችን አዘጋጅቷል። ተሻሽሎ የቀረበውም በ2011 ዓ.ም. ነው።
  • የመንግስት ባለስልጣን መስሪያ ቤቶች፡- የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (ኢመአ)፣ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን (አአመባ)፣ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን (አአውፍባ) እና የመሳሰሉት ከላይ ከተጠቀሱት ደረጃዎች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ወይም የተወሰነ ማሻሻያ የተደረገባቸው ውሎች ለፕሮጀክቶቻቸው ይጠቀማሉ።

በፕሮጀክቱ የሥራ ወሰን እና ሌሎች መስፈርቶች ላይ በመመስረት፤ አንድ ባለሙያ ከላይ በተጠቀሱት ደረጃዎች መሰረት የግንባታ ውል ሰነድ ማዘጋጀት ይችላል። ሰነዶቹን ለማርቀቅ ጥሩ የቴክኒክ እና የህግ እውቀት ያስፈልጋል።

የኮንትራት ሰነዶችን ለማዘጋጀት ምን አይነት ጥሩ ተሞክሮዎች ያስፈልጋሉ?

በአጠቃላይ የግንባታ ሰነዶችን ለማርቀቅ እና ለማዘጋጀት የሚከተሉት ተሞክሮዎች ተመራጭ ናቸው።

ግልጽ ወይም ግራ የማያጋባ ቋንቋ መጠቀም፡- እንደ “ምክንያታዊ”፣ “ተጨባጭ” ወይም “አጥጋቢ” ያሉ ግልጽ ያልሆኑ ቃላት የኮንትራት አጥፊ ቋንቋዎች ናቸው። ለተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ነገር ማለት ሊሆን ይችላል። በተቻለ መጠን ግልጽ ቋንቋ በመጠቀም ያስተካክሉ። ለምሳሌ "በጊዜው ማጠናቀቅ" ከማለት ይልቅ "ፈቃድ ከፀደቀ በ 45 ቀናት ውስጥ ማጠናቀቅ" አስተካክለው ይፃፉ።
የተሟላ እና የተነተነ የስራ መግለጫዎችን ማካተት፡- አጭር እና ግልጽ ያልሆነ የስራ መግለጫ እንደዚህ ይመስላል፡ "ኮንትራክተሩ ወጥ ቤቱን ያድሳል።" አንድ ጠንካራ የስራ መግለጫ እያንዳንዱን ስራ መተንተን አለበት: የማፍረስ ሂደት፤ የሚገጠመው ዕቃ ስም፣ ሞዴል፣ እና ቀለም፤ የዓገጣጠም ዘዴ፤ እና የሙከራ ሂደት።
የኢንሹራንስ እና የማስያዣ መስፈርቶችን ያካትቱ፡- የመድን ሽፋን መስፈርቶች ማሟላት የሚመከሩ ብቻ አይደሉም - ለድርድር የማይቀርቡ ግዴታዎች ናቸው።
አስፈላጊ የለውጥ አስተዳደር ድንጋጌዎች፡- ለውጦች በእያንዳንዱ ፕሮጀክት ላይ ይከሰታሉ። ውልዎ እነሱን ለማስተናገድ የማይበገር ሂደት ያስፈልገዋል። ደካማ የለውጥ አስተዳደር ወደሚከተለው ይመራል፡- ያልተከፈለ ሥራ፣ የጊዜ ሰሌዳ መዘግየት፣ የግንኙነቶች መፍረስ፣ “በተካተተው” ላይ አለመግባባቶች።
ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ መርሃ ግብሮችን ያዘጋጁ፡- ብልጥ መርሐግብር ማለት፡ ለፈቃድ መዘግየቶች ጊዜ የሚተው፤ የቁሳቁስ አቅርቦት ጊዜን ግምት ውስጥ የሚያስገባ፤ የአየር ሁኔታ ተፅእኖዎችን ማቀድ፤ እና የባለቤት ውሳኔ ቢሮክራሲ ታሳቢ ማድረግ አለበት።

ከታች ባለው የአስተያየት መስጫ ሳጥን በኩል ሃሳብዎን ያካፍሉ።

ወይም

አስተያየቶች

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው