🏗️ Contractor Vs Owner: Two Real Disputes Without Written Agreements ⚖️ - Construction Solution Ideas

🏗️ ተቋራጭ ከባለቤት፡ ሁለት የግንባታ አለመግባባቶች ያለምንም የጽሁፍ ውል ⚖️

መግቢያ የውይይት መድረኮች የግንባታ ኮንትራት 🏗️ ተቋራጭ ከባለቤት፡ ሁለት የግንባታ አለመግባባቶች ያለምንም የጽሁፍ ውል ⚖️

  • This topic is empty.
Viewing 1 post (of 1 total)
  • Author
    Posts
  • #1288

    ሁለት እውነተኛ ታሪኮች፣ ሁለት የግንባታ አለመግባባቶች እና አንድ የተለመደ ስህተት — የጽሑፍ ውል የለም።.

    🔹 1ኛ ጉዳይ – አቶ አለሙ እና መንግስቱ ጠ/ተቋራጭ
    አቶ አለሙ አሪፍ ቤት ሰርቶ ነሐሴ ላይ ለመግባት አቅዶ ነበር። ነገር ግን በወለልና ግድግዳ ላይ ስንጥቅ በማየቱ፤ መንግስቱ ጠ/ተቋራጭ ኢንዲጠግንለት ይቀጥረዋል የጽሁፍ ውል የለም። አለሙ ለመንግስቱ “ስለ ክፍያ ምንም አትጨነቅ፣ በፍጥነት ስራውን ጨርስ” ይለዋል።

    • መንግስቱ ጠ/ተቋራጭ ተጨማሪ ባለሙያዎችን አሳትፎ ቤቱን ጠግኖ ይጨርሳል።
    • አለሙ የመጀመሪያዎቹን ሶስት ክፍያዎች ለመንግስቱ ጠ/ተቋራጭ ከፍሏል።
    • መጨረሻው ክፍያ ላይ መንግስቱ 20 በመቶ ትርፍ እና 10% ትርፍ ጨምሮ የክፍያ ጥያቄ ላከ።
    • አቶ አለሙም “ይህን አልከፍልም!” በማለት ፈቃደኛ አልሆነም።

    🔹 2ኛ ጉዳይ – ወ/ት ሰብለ እና ታሜክስ ህ/ተቋራጭ
    ወ/ሪት ሰብለ በከፊል የተጠናቀቀ G+5 የንግድ ህንፃ ገዝተው ሁለት ተጨማሪ ወለሎች ወደ ላይ መጨመር ያስባሉ። ታሜክስ ህ/ተቋራጭ በ10 ሚሊየን ብር ስራውን እንዲሰሩ በቃል ይስማማሉ - የጽሁፍ ውል፣ የስራ መጠን፣የጊዜ ገደብ እና መመዘኛ መመሪያዎች የሉም።

    • ታሜክስ ህ/ተቋራጭ አንድ ወለል ከጨረሰ በኋላ፣ የ10 ሚሊዮን ክፍያ መጠየቂያ ይልካል።
    • ወ/ሪት ሰብለ “ይህ የብር መጠን ለሁለት ወለል እንጂ ለአንድ አይደለም!” ስትል ክፍያውን አልቀበልም ትላለች።
    • ወ/ሪት ሰብለ ለመክፈል ፈቃደኛ ስላልሆነች ታሜክስ ህ/ተቋራጭ ሥራውን ያቆማል።

    ሁለቱም ጉዳዮች ከባድ ጥያቄዎችን ያስነሳሉ -

    • እነዚህ አለመግባባቶች ወደ ፍርድ ቤት መሄድ አለባቸው ወይንስ ውጭ መፍትሄ ያገኛሉ?

    • ትክክለኛው ማነው - ባለቤት ወይም ኮንትራክተሩ?

    • የቃል ስምምነቶች ሁለቱንም ወገኖች ሊከላከሉ ይችላሉ?

    አስተያየትዎን እና ክርክርዎን ለሌሎች አባላት ያካፍሉ።

    📢 ብይኑ በ15 ቀናት ውስጥ እዚህ ይፋ ይሆናል። ተከታተሉት!

Viewing 1 post (of 1 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.