ለመተማመን፦ ቀላል የግንባታ ስምምነት ማዘጋጀት

Drafting construction agreement

Are you planning to ቤትዎን ለማደስ ወይም ለመጠገን እያሰቡ ነው? ወይም አዲስ አጥር ሊገነቡ ነው? ወይም የውጭ ደጅዎትን በቴራዞ ሊሸፍኑ ነው? ወይም ለዝናብ ጎርፍ ትቦ መውረጃ ሊሰሩ ነው? ወዘተ. ወይስ እነዚህን ስራዎች ለመስራት ተቋራጭ ሆነዋል።

እነዚህን ፕሮጀክቶች ለመጀመር ጠቃሚ እና ብልህ መንገድ እንዳለ ብነግርዎስ? ቀላል የግንባታ ውል ስምምነትን ማዘጋጀት።

On our article “Understanding Construction Contract Agreements: A Beginner’s Guide”, we have discussed construction contract agreement briefly and why it is very important to your construction work. We also categorized projects based on their complexity as ቀላል፣ ትንሽ፣ መካከለኛ እና ትልቅ ብለን መድበናል። ከላይ ያሉት ሥራዎች እና የመሳሰሉት ቀላል ፕሮጀት ውስጥ ይመደባሉ።

ስለዚህ ቀላል የኮንትራት ስምምነት እንዴት ማዘጋጀት እንደሚችሉ እናሳዮታለን። ይህ ስምምነት ፕሮጀክትዎ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ መተማመን እና እርግጠኛነትን ይፈጥራል።

በእርግጥ የግንባታ ውል ስምምነት ያስፈልገዎታል?

ምናልባት የግንባታ ውል ስምምነት ለምን ያስፈልገኛል ብለው አእየጠየቁ ይሆናል። የጥያቄዎት ምክንያት ደግሞ:-

እኔ የምሰራው 20 ሜትር የግንብ ቦይ ሲሆን አንድ ግንበኛ ብቻ ነው የሚፈልገው

G+2 የመኖሪያ ሕንፃ ነው እየገነባሁ ያለሁት እና ሥራ ተቋራጩ የወንድሜ የቅርብ ጓደኛ ነው

በከተማ ውስጥ በጣም ታዋቂ/ስመጥር ለሆነ ሀብታም ሰው ነው የምገነባው

ከመንግሥት መሥሪያ ቤት ጋር ነው የምሰራው፤ ሥራ አስኪያጁ ያለስምምነት ሥራ እንድጀምር ነግረውኛል

ብዙ አይነት ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል። መልሱን በሚከተሉት በጣም ቀላል በሆኑ ጥያቄዎች መመለስ ይችላል። የሚከተሉት ነገሮች ቢከሰቱ ምን ይሰማዎታል?

በ3 ወር እንዲጠናቀቅ የታሰበው ቤት 3 ፈጅቶ አሁንም በግንባታ ላይ ቢሆን

ጓደኛህ ሥራ ተቋራችጭ የቅድሚያ ክፍያ (ቀብድ) ወስዶ ቢጠፋ

ሀብታም ዘመድዎ ገንብተው ላጠናቀቁት ሕንፃ ለመክፈል ፈቃደኛ ባይሆን

የተሰራው ግንብ ቦይ በጎርፍ ቢወሰድ

ዓለማችን ከላይ በተጠቀሱት እና ተመሳሳይ ጉዳዮች የተሞላ ነው። እና እነዚህ ሁኔታዎች ያጋጠማቸው ሰዎች ለንዴት፣ ለብስጭት፣ እና ለቁጭት ተዳርገዋል። ስለዚህ የግንባታ ሥራዎ የኮንትራት ስምምነት ያስፈልገዋል? ትክክለኛው እና ግልጹ መልስ አዎ ነው!

ታዲያ ለፕሮጀክቴ የግንባታ ውል ስምምነት እንዴት ማርቀቅ እችላለሁ?

ለቀላል ፕሮጀክትዎ የውል ስምምነት ማዘጋጀት አስቸጋሪ አይደለም። የሚከተሉትን ጥያቄዎች በወረቀት ላይ ይመልሱ፦

  • የፕሮጀክቱ ባለቤት እና ሥራ-ተቋራጭ (ኮንትራክተር) ማን ነው? ለእያንዳንዱ ወገን ሰነዶችን አያይዝ

ለምሳሌ፡- ጊዜው ያላለፈበት መታወቂያ፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ እና የመሳሰሉት

  • ምንድን ነው መገንባት ያሰቡት? ስለሚሠራው ሥራ በግልፅ ቋንቋ ይጻፉት።

ለምሳሌ: "በቤቴ ዙሪያ የብሎኬት አጥር ማሰራት እፈልጋለሁ፤ ከጎረቤቴ አጥር ቁመት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፤ ጥራት ባለው ብሎኬት ይሰራልኝ፤ የአጥሩ ቀለም ግራጫ ይሁን፤ እና ሁሉም ተረፈ ምርቶች በመጨረሻ መወገድ አለባቸው።"

  • የግንባታ ዋጋው ስንት ነው? ምናልባት ጓደኛዎን ፣ ዘመድዎን ይጠይቁ ወይም የእኛን የውይይት መድረክ ይቀላቀሉ።

ለምሳሌ፡- “የግንባታ ቁሳቁስ እርሶ ካቀረቡ፤ የሥራ ተቋራጩን የጉልበት ዋጋ ማወዳድር ያስፈልጋል”

  • መቼ እንዲጠናቀቅ ይፈልጋሉ? ተግባራዊ ሊሆን የሚችል የጊዜ ሰሌዳ ያዘጋጁ።

ለምሳሌ፡- “በ1 ወር ወይም ሁለት ሳምንት ጊዜ እንዲጠናቀቅ እፈልጋለሁ”

  • የክፍያ ሁኔታዎች ምን ምንድን ናቸው? የክፍያው ሁኔታ ቅድመ ክፍያ እና የመጨረሻ ክፍያ ቢሆን ይመረጣል።

ለምሳሌ፡- “40% እንደ ቅድመ ክፍያ እና ስራ ሲጠናቀቅ ደግሞ 60% መክፈል ይቻላል”

ከታች በምስሉ ላይ እንደሚታየው፤ ከላይ የተገለጸውን ሀሳብ ሊሞላ ወደ ሚችል ቅፅ ቀይረነዋል።

ለ5ቱ ጥያቄዎች ያዘጋጁት መልሶች በምስሉ ላይ ባለው የስምምነት ቅፅ ባዶ ቦታዎች ላይ በመጻፍ ውሉን ማዘጋጀት ይቻላል። እባኮትን የተመረጡ፣ ግራ የሚያጋቡ ወይም ህጋዊ ቃላትን በመጠቀም የሚያምታታ ሀሳብ እንዳያሰፍሩ። ሁሉም ሰው እንዲረዳው፤ ከላይ የሚታየው የውል ስምምነት በጣም ግልጽ እና ቀላል በሆነ ቋንቋ መፃፍ አለበት።

መደምደሚያ

ከላይ የሚታየውን የግንባታ ውል ስምምነት ማዘጋጀት ለቀላል የግንባታ ፕሮጀክቶች የሚከተሉት ጥቅሞች አሉት።

  • እውነተኛ ድርድር እስከተደረገ ድረስ፤ የፕሮጀክቱን የሥራ መጠን ለባለቤቱና ለገንቢው በደንብ ይገለጻል።
  • የፕሮጀክቱ ዋጋም በቁጥር ይቀመጣል።
  • የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜም ይታወቃል።
  • አለመግባባት ቢፈጠር እንኳ ህጋዊ ተቀባይነት ያለው ሰነድ ነው።

ግንባታ በሚያከናውነው አካል እና በሚያሰራው አካል መካከል አለመግባባቶች ሊፈጠሩ ይችላል። እነዚህን አለመግባባቶች ለመፍታት የሚመረጠው መንገድ ውይይት እና ድርድር ነው።

ነገሮች እንደታቀደው ካልሄዱ ከላይ ያሳየነው ቀላል ውል አዘገጃጀት ከብዙ ችግር ያድንዎታል። ከላይ ያለውን ስምምነት በእጅ ለመጻፍ ብቻ ነጭ ወረቀት እና እስክሪብቶ መጠቀም ይችላሉ።

በመጨረሻም ትናንሽ ፕሮጀክቶች፣ እንደ የቤት እድሳት/ጥገና፣ የመኖሪያ ቪላ/ህንጻ ግንባታ፣ አነስተኛ የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና አነስተኛ ድልድይ ግንባታዎች፤ በባለሙያ የተዘጋጀ ኮንትራት ስምምነት ውል እና ሰነዶችን ይፈልጋሉ። በዚህ አርዕስት ላይ የጻፍነውን ጽሑፋችንን ማንበብ ከፈለጉ ትናንሽ ፕሮጀክቶች፤ ትልቅ ግልጽነት፡ የግንባታ ኮንትራቶችን ማዋቀር.

ከታች ባለው የአስተያየት መስጫ ሳጥን በኩል ሃሳብዎን ያካፍሉ።

ወይም

አስተያየቶች

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው