ትናንሽ ፕሮጀክቶች፤ ትልቅ ግልጽነት፡ የግንባታ ኮንትራቶችን ማዋቀር

residential building under completion

G+3 የመኖሪያ ሕንፃ ለመገንባት ኢንቨስት ሊያደርጉ ነው፤ ወይስ በመንደር ውስጥ አነስተኛ ድልድይ ለመሥራት የኮንትራት ሥራ ወስደዋል፤ in a village, or set up a ወይም ምናልባት ለፋብሪካዎ መጋዘን ለመስራት አቅደዋል። እነዚህ ትናንሽ ፕሮጀክቶች ቀላል ሊመስሉ ይችላሉ። ነገር ግን ግልጽ ስምምነት ከሌለ፤ በፍጥነት ወደ ውስብስብነት፤ መዘግየቶች ወይም አለመግባባቶች ይሸጋገራሉ። ይህ ጽሁፍ ለትንንሽ ፕሮጀክቶች የግንባታ ውል አስፈላጊነትን እና ስምምነቱን እንዴት ማርቀቅ እንደሚቻል ያትታል - ይህን ውል በማዘጋጀት በራስ መተማመን መገንባት ይችላሉ።

ወደዚህ ርዕሰ ጉዳይ ከመግባታችን በፊት፤ የግንባታ ኮንትራቶችን አስፈላጊነት እና ዓይነቶችን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ጽሑፎቻችን ውስጥ ተመልክተናል።

አንድ ሰው መረዳት አለበት፤ ትናንሽ ፕሮጀክቶች እንደ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ውስብስብ እና አስቸጋሪ መሆናቸውን ነው። ልዩነቱ ትንንሽ ፕሮጀክቶችን ከአንድ ወይም ሁለት ባለሙያዎች ጋር በመሆን ፕሮጀክቱን መረዳትና በማስተዳደር መቻሉ ብቻ ነው። የሚከተሉት ነጥቦች በግንባታ ላይ ልምድ ለሌላቸው ወይም ባለሙያ ላልሆኑ ሰዎች በጣም አስፈላጊ ናቸው።

  1. የቡድን ስራ፡ ግንባታ የአንድ ሰው ሥራ አይደለም!
  2. ዕቅድ፡ ግንባታ ስልታዊ ዝግጅት ያስፈልገዋል።
  3. በጀት፡ የግንባታ ሥራ ብዙ ገንዘብ ይጠይቃል።
  4. የጊዜ አጠቃቀም፡ የተጠና የጊዜ ሰሌዳ እና መርሃ ግብር ፕሮጀክትን በጊዜ ለማጠናቀቅ ወሳኝ ናቸው።
  5. ጥራት ቁጥጥር፡ በግንባታ ላይ ጥራትን ማረጋገጥ እና መቆጣጠር ያስፈልጋል።
  6. ሰነዶች፡ ሪፓርቶች እና መዝገቦችን ሰንዶ መያዝ ግድ ነው።

ይህ ጽሁፍ የፕሮጀክትዎ እቅድ እና ንድፍ ተጠናቆ እና በደንብ ተሰንዶ እንዳለቀ ታሳቢ በማድረግ ነው የተጻፈው። ግንባታ ከመጀመርዎ በፊት በደንብ የተዘጋጀ እና የተፈረመ የግንባታ ስምምነት ያስፈልግዎታል።

ታዲያ ለፕሮጀክቴ የግንባታ ውል ስምምነት እንዴት ማርቀቅ እችላለሁ?

የዚህ ጥያቄ መልስ፡- እርስዎ የኮንትራት መሐንዲስ ወይም የግንባታ ጠበቃ ካልሆኑ በስተቀር ስምምነትዎን አያዘጋጁም። unless you are a contract engineer or construction lawyer. ነገር ግን በስምምነቱ ላይ ስለምትፈርሙ፤ ስምምነቱን በደንብ መረዳት ይኖርቦታል። የሚከተሉት ክፍሎች የግንባታ ስምምነቶችን የተለያዩ ገጽታዎች ያብራራሉ እና በመጨረሻም እንደ ፕሮጀክቶ ፍላጎት ሊሚሻሻሉ የሚችሉ አብነቶችን እናቀርባለን።

በግንባታ ስምምነት ውስጥ የሚሳተፉ ቁልፍ አካሎች/ተዋናዮች

የግንባታ ኮንትራት ውስጥ ብዙውን ጊዜ ብዙ ተዋናዮች ይኖራሉ፡

  • ባለቤት/ደንበኛ፡- የፕሮጀክቱን ወጪ የሚሸፍነው ሰው ወይም ድርጅት
  • ሥራ ተቋራጭ፡- ለዕለት ተዕለት ሥራዎች ኃላፊነት የሚወስደው እና ግንባታውን የሚያከናውነው
  • አርክቴክቶች/መሐንዲሶች፡- የንድፍ እና የቁጥጥር ባለሙያዎች

ዋና የግንባታ ኮንትራት ውል ዓይነቶች

ማንኛውንም ውል ከማዘጋጀቱ በፊት፤ ምን አይነት የግንባታ ውል እንደምንጠቀም መወሰን ያስፈልጋል። ከላይ በጠቀስነው ጽሁፋችን ላይ እንደተገለፀው አምስቱ ዋና የግንባታ ውሎች የሚከተሉት ናቸው።

ቁርጥ ወይም ቋሚ ዋጋ ኮንትራት ውል

የነጠላ ዋጋ ኮንትራት ውል

የጊዜ እና ግብዓቶች ኮንትራት ውል

ወጪ እና ተጨማሪ ክፍያ ኮንትራት ውል

የንድፍ-ግንባታ ኮንትራት ውል

የግንባታ ኮንትራቶች የሚዘጋጁበት የሕግ ማዕቀፎች

የግንባታ ኮንትራቶች የሕግ ማዕቀፍ እንዲኖራቸው ያስፈልጋል። እነሱ የሚቀረጹት በሚከተሉት ነው:

  • የአካባቢ የመሰረተ ልማት ወይም የግንባታ ደንቦች እና መተዳደሪያዎች
  • የኢንዱስትሪ ደረጃዎች እና ምርጥ ተሞክሮዎች
  • የውል ሕግ መርሆች
  • የፍቃድ መስፈርቶች

የተለያዩ ቦታዎች የተለያዩ ደንቦች አሏቸው. ለዚያም ነው እነዚህን ስምምነቶች በሚረቅቁበት ጊዜ ክልላዊ ዕውቀት ማግኘቱ ወሳኝ የሆነው።

የኮንትራት ውል ዋና ዋና ክፍሎች

በሚፈረመው ሰነድ ውስጥ የሚካተቱት የግንባታ ውል ዋና ዋና ክፍሎች የሚከተሉት ናቸው።

የፕሮጀክት ዝርዝር መግለጫ፡ - የፕሮጀክት ስም እና መለያ ኮድ መወሰን። የፕሮጀክቱ አከባቢ ልዩ ቦታ እና የሚሳተፉ አካላት (ባለቤት, ተቋራጭ, አማካሪ እና የመሳሰሉት) ተለይተው መታወቅ አለባቸው።
የሥራው መጠን፡- ሁሉም ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች፣ ጉልበት እና ባለሙያዎች በዝርዝር መታወቅ አለበት። የንድፍ ሰነዶች፣ ዝርዝር መግለጫዎች፣ እና ሁሉም ሪፖርቶች ተዘጋጅተው መቅረብ አለባቸው።
ተግባራት እና ኃላፊነቶች: - ማን ለምን ተጠያቂው ነው? ግዴታዎች እና ሀላፊነቶች ለእያንዳንዱ የውል አካል መመደብ አለባቸው።
የክፍያ አከፋፈል:- አጠቃላይ የግንባታ ወጪ ተገምቶ ስምምነት መደረግ አለበት። መቼ ክፍያዎች እንደሚፍጸሙ፣ ምን ያህል ቅድመ ክፍያ እና መያዣ እንደሚያስፈልግ፣ የመክፈያ ዘዴ፣ ወዘተ.
የፕሮጀክት መርሃ ግብር፡- ፕሮጀክቱ መቼ እንደሚጀመር እና መቼ እንደሚጠናቀቅ የጊዜ ሰሌዳውን ግልጽ ማድረግ ያስፈልጋል። መዘግየት ቢከሰት እና የማጠናቀቂያ ቀንን እንዴት ማራዘም ይቻላል?
የግንባታ ለውጥ ትዕዛዞች:- በግንባታ ወቅት በንድፍ ማስተካከያ ወይም በመንግስት መስፈርቶች መሻሻል ምክንያት ለሚመጡ ለውጦችን እንዴት ማስተናገድ እንደሚቻል ማወቅ አለብን። የዚህን ለውጥ ዋጋ መገመት ይኖርብናል።
የግንባታ ጥራት፡ - የግንባታውን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል ዘዴ መቀየስ ያስፈልጋል። የጥራት ማረጋገጫን በተመለከተ ደረጃዎችን እና መመሪያዎችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል።
አለመግባባቶች፡- አለመግባባቶችን ለመፍታት ግልፅ የሆነ ሂደት መቀመጥ አለበት።
ውል ማቋረጥ፡- የግንባታ ፕሮጀክቶ የተለያዩ ተግዳሮቶች ሊያጋጥሙት ይችላል፤ ይህም በአንድ ወገን ወይም በሁለቱም ወገኖች ውሉ እንዲቋረጥ ሊያደርግ ይችላል። ውል ማቋረጫ መስፈርቶች ማዘጋጀት እና መንደፍ አስፈላጊ ነው።

ለእነዚህ ክፍሎች የተዘጋጀው መግለጫ ጠቅለል ተደርጎ ወደ ስምምነት ሊዋቀር ይችላል።

የግንባታ ውልዎን ማርቀቅ እና ማዘጋጀት.

የግንባታ ውል ሰነድዎን ለማዘጋጀት ሁለት አማራጮች አሉ።

አማራጭ ሀ

የውል ባለሙያ መቅጠር እና ከላይ ያዘጋጁትን የፕሮጀክቱን መግለጫ ይስጡት። ባለሙያው ረቂቅ ሰነድ ያዘጋጅልዎታል።

አማራጭ ለ

በተጨማሪም ከዚህ ድህረ ገጽ ናሙና አብነቶችን ማግኘት ይችላሉ። እነዚህ አብነቶች የተነደፉት ለመኖሪያ ሕንፃ፣ ለትንሽ ድልድይ እና የውስጥ መንገዶች ነው። እነዚህ አብነቶች ከባለሙያ ጋር በመሆን ተገቢውን ማስተካከያ በማድረግ ረቂቅ ሰነድ ማዘጋጀት ይችላሉ።

ክለሳ

ለትንሽ ፕሮጀክትዎ በጥንቃቄ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፤ ለሁሉም የግንባታ አካላት ትልቅ ግልጽነት ይፈጥራል። በፕሮጀክትዎ ውስጥ ባለሙያ ማካተት እና ማሳተፍም አስፈላጊ ነው። በፕሮጀክትዎ ላይ በደንብ የተዘጋጀ እና የተፈረመ የግንባታ ውል ሰነድ፤ በጊዜ ሂደት ሊመጡ ከሚችሉ የተለያዩ ችግሮች፣ መዘግየቶች ወይም አለመግባባቶች ያድንዎታል።

ከታች ባለው የአስተያየት መስጫ ሳጥን በኩል ሃሳብዎን ያካፍሉ።

ወይም

አስተያየቶች

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው