መለያ፥ formwork and falsework

  • 10 Quality Tests You Should Never Skip in Your Building Project

    በግንባታ ፕሮጀክትዎ ውስጥ ፈጽሞ መዝለል የሌለብዎት 10 የጥራት ማረጋገጫዎች

    መግቢያ፦ አንድ የተዘለለ የጥራት ማረጋገጫ ለአመታት ኪሳራ ሊዳርጎት ይችላል

    በመሃል አዲስ አበባ በደራው ከተማ፣ ከመሬት የሚወጣ የጂ+10 ሕንፃ የኮንክሪት እና የፌሮ ብረት ስብጥር ብቻ አይደለም። የዓመታት ቁጠባ፣ የገንቢ ራዕይ እና ብዙውን ጊዜ የቤተሰብን የዕድሜ ልክ ኢንቨስትመንት ነው።

    ነገር ግን በዛሬው የኢትዮጵያ የግንባታ ገበያ - የሲሚንቶ እና የፌሮ ዋጋዎች በየሳምንቱ የሚለዋወጡበት እና የፕሮጀክት የጊዜ ሰሌዳዎች ጥብቅ በሆነበት - ብዙዎች አደገኛ አቋራጭ መንገድ ይፈልጋሉ፤ ገንዘብ እና ጊዜ ለመቆጠብ የጥራት ማረጋገጫዎችን መዝለል/መተውን እንዳማራጭ ይወስዳሉ።

    በብልሃት ይገንቡ። የግንባታውን ደህንነት ይጠብቁ። አንድ ጊዜ ብቻ ይገንቡ።

    ያለ ጥራት ማረጋገጫዎች የተከናወነ ግንባታ የተለመዱ ችግሮችን ያጋጥሙታል - በኢትዮጵያ የተሰነጠቁ ግድግዳዎች፣ በሰንጋተራ ውስጥ ትልቅ የአርማታ ምሶሶ መፍረስ፣ በአቃቂ ላይ የተበላሸ ግንባታ፣ የአዲስ አበባ የመዋኛ ገንዳ ዋሃ ስርገት ችግር እና አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አበይት ዜና የሚሆኑ የመዋቅር ውድቀቶች ያጋጥማሉ።

    Ware house wall in Ethiopia cracked due to foundation problem

    ከሚከተሉት አንዱ ቢሆኑ፡

    • የእድሜ ልክ ቁጠባዎን በማፍሰስ እየገነቡ ያሉ የፕሮጀክት ባለቤት
    • የብዙ ሚሊዮን ብር በጀት የሚያስተዳድር የፕሮጀክት ሃላፊ
    • ለመጀመሪያ ጊዜ በመስክ ስራ ላይ የተሰማራ አዲስ ተመራቂ

    በፍጹም መዘንጋት የሌለቦት የግንባታዎ የወደፊት ደህንነት ማስተማመኛዎች አሉ፡ የጥራት ማረጋገጫዎች።.

    ይህ ጥሩ ልምምድ ብቻ ሳይሆን - የኢትዮጵያ የግንባታ አዋጅ ቁጥር 1356/2024 የጥራት ቁጥጥርን እንደ ህጋዊ መስፈርት ያስቀምጠዋል።

    ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ስኬታማ ፕሮጀክቶችን ከውድቀት የሚያድኑ አስፈላጊ የጥራት ማረጋገጫዎች ናቸው - ከእውነተኛ የግንባታ ስራ ተሞክሮዎች ጋር ተገልፀዋል።


    1. ግንባታ ከመጀመሩ በፊት በከናወን ያለበት የአፈር ምርመራ — የግንባታዎ የመጀመሪያ የኢንሹራንስ ፖሊሲ ነው

    ለምን አስፈላጊ ሆነ

    እያንዳንዱ የመዋቅር ዲዛይን የሚጀምረው በአፈር/መሬት የመሸከም አቅም ጥናት ነው። የአፈር/መሬት መረጃ የተሳሳተ ከሆነ፣ አጠቃላይ የመሠረት ዲዛይኑ ግምታዊ ይሆናል። ውጤቱም የህንፃ መስጠም/ማዘንበል፣ ስንጥቆች እና ከባሰ ደግሞ ከዓመታት በኋላ የመዋቅር አለመረጋጋት/ውድቀት ያስከትላል።

    መከተል ያለብዎት ትክክለኛ የምርመራ ሂደቶች

    • የግንባታ ቦታ እና አካባቢ ጥናት እና መረጃ ማሰባሰብ
    • የመስክ ምርመራ (trial pits or boreholes)
    • በመስክ ላይ የሚሰሩ ምርመራዎች
    • የላቦራቶሪ አፈር ምርመራ
    • የጂኦቴክኒካል ሪፖርት በብቃት ባለው መሐንዲስ

    የተለመዱ ትክክል ያልሆኑ አሰራሮች

    • በአቅራቢያ ያሉ ፕሮጀክቶችን አፈር ምርመራ ሪፖርቶችን መጠቀም
    • የግንባታ ቦታዎን ከማስመርመር ይልቅ በኮንትራክተር ወይም በጓደኛ ምክር ላይ መተማመን

    የባለሙያ ምክር

    ለአነስተኛ የመኖሪያ ሕንፃዎች እንኳን የአፈር ምርመራ ያወጡት እያንዳንዱ ብር ከፍተኛ ዋጋ አለው። የመሠረት ጥገና ከዛሬው የአፈር ምርመራ ዋጋ ሲነፃፀር ብዙ እጥፍ ወጪ የሚጠይቅ ነው።


    2. ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ጠጠሮች እና ውሃ — ኮንክሪት ጥንካሬ እንደ ግብዓቶቹ ጥራት ይወሰናል

    ለምን አስፈላጊ ሆነ

    ኮንክሪት ቀላል ድብልቅ ነው። አንዱ ግብዓት ደካማ ከሆነ መላው መዋቅር ይጎዳል። የቆሸሸ አሸዋ፣ ደካማ ጠጠሮች ወይም የተበከለ ውሃ ሳይታወቅ ጥንካሬውን ይቀንሱታል።

    አስፈላጊ የጥራት ምርምሮች

    • የአሸዋ ቅንጣቶች መጠን እና ንፅህና
    • የጠጠር ጥንካሬዎች ማረጋገጫ
    • የውሃ ጥራት ማረጋገጫ

    የተለመዱ ትክክል ያልሆኑ አሰራሮች

    • አሸዋ በጭቃማ መሬት ላይ ማከማቸት
    • የተበከለ ውሃ መጠቀም
    • ጠጠር በኮን ቅርፅ መከመር የመጠን መለያየትን ያስከትላል

    የባለሙያ ምክር

    • ሁልጊዜ ንጹህ ውሃ ይጠቀሙ
    • ጠጠርን በተደላደለ ሁኔታ እና ንፅህ ቦታ ላይ አከማቹ
    • አሸዋውን ከአፈር ብክለት ነፃ ያድርጉት

    3. የፎርም ወርክ እና የፎልስ ወርክ ማረጋገጫ - የመዋቅርዎ ቅርፅ እና ደህንነት

    ለምን አስፈላጊ ሆነ

    ፎርም ወርክ ለኮንክሪት ቅርፅ ይሰጣል። ፎልስ ወርክ (ስካፎልዲንግ እና ጊዜያዊ ድጋፎች) ኮንክሪቱ እስኪጠነክር ድረስ ሙሉውን የእርጥብ ኮንክሪት ክብደት ይይዛል። ከሁለት አንዱ ደካማ፣ የተሳሳተ አቀማመጥ ካለው ወይም ያለጊዜው ከተወገደ ያዘበዘቡ ወለሎች፣ የተጣመሙ አምዶች፣ የገጽታ ጉድለቶች - ወይም ከከፋ ኮንክሪት በሚሞላበት ወቅት ሊደረመስ ይችላል።

    ሁልጊዜ ያረጋግጡ

    • የፎርም ወርክ አቀማመጥ፣ ውሃ ልክ እና ቋሚዎች
    • አርማታ እንዳይንጠባጠብ ጥብቅ መገጣጠሚያዎችን ያረጋግጡ
    • በቂ የሆነ ማጠናከሪያ እና የድጋፍ ክፍተት
    • ከሙሊት በፊት ፊት ገፁን ማጽዳት
    • የማላቀቂያ ዘይት በአግባቡ መቀባቱን
    • የፎልስ ወርክ ክብደት የመሸክም አቅም እና መቋቋም
    • ደህንነቱ የተጠበቀ የስራ ቦታ እና መተላለፊያ

    የተለመዱ ትክክል ያልሆኑ አሰራሮች

    • የተበላሸ ወይም የተሰበረ የፕላይ እንጨት እንደገና መጠቀም
    • የወለል ፎርም ወርክ በቂ ያልሆነ ትስስር
    • ኮንክሪት አስፈላጊውን ጥንካሬ ላይ ከመድረሱ በፊት ድጋፉን መንቀል
    • መቆሚያ ሳያዘጋጁ ደካማ መሬት ላይ የፎርም ወርክ ድጋፎችን ማቆም

    የባለሙያ ምክር

    • ከእያንዳንዱ ኮንክሪት ሙሊት በፊት ፎርም ወርኩን ይፈትሹና እና ያረጋግጡ
    • ያለ ባለሙያ ፈቃድ ፎልስ ወርክ በጭራሽ አያፍርሱ
    • የፎርም ወርክ ሥራ ፍተሻ ዝርዝር ቅጽ በግንባታ ቦታ ላይ ያስቀምጡ
    • አናጢዎችንና ፎርማኖችን በትክክለኛው የድጋፍ አቀማመጥ ላይ ማሰልጠን

    4. የአርማታ ፌሮ ፍተሻ — ብረት ኮንክሪት ከመሞላቱ በፊት በትክክል መቀመጥ አለበት

    ለምን አስፈላጊ ሆነ

    ኮንክሪት አንዴ ከተሞላ በኋላ የፌሮ ስህተቶች ዘላቂ ናቸው። ደካማ ጥራት ያለው ብረት ወይም የተሳሳተ አቀማመጥ፤ ከባድ ጭነት ወይም የመሬት መንቀጥቀጥ በሚከሰትበት ጊዜ ድንገተኛ ውድቀት ሊያስከትል ይችላል።

    ሁልጊዜ ያረጋግጡ

    • የፌሮ መሳሳብ እና የመታጠፍ ምርምራዎች
    • የፌሮ ውፍረት እና አቀማመጥ ስፋት
    • የትስስር ርዝመት እና ጥልፍልፍ
    • ትክክለኛ የኮንክሪት ሽፋን
    • ንጹህ፣ ዝገት የሌለባቸው ፌሮዎች

    የተለመዱ ትክክል ያልሆኑ አሰራሮች

    • ያልተፈተሸ ብረት መጠቀም
    • ጊዜ ለመቆጠብ ምርመራ/ፍተሻ መተው

    የባለሙያ ምክር

    ኮንክሪት ከሞሞላቱ በፊት፤ የ30 ደቂቃ ፍተሻ ማድረግ ከዓመታት በኋላ ሊከሰት የሚችልን የመዋቅር አደጋን ይከላከላል


    5. የኮንክሪት ስለምፕ እና የኩብ ጥንካሬ ምርመራዎች - ይመኑ፣ ግን ያረጋግጡ

    ለምን አስፈላጊ ሆነ

    ኮንክሪት የህንፃዎ ዋና መሠረት ነው። በመስክ ላይ የኮንክሪት ቡኮ፣ የውሃ መጠን ወይም የመጠንከር ሂደት ችግር ካለው በወረቀት ላይ የተቀመጠው የዲዛይን ጥንካሬ የማይጠቅም ቁጥር ነው።

    የስለምፕ ምዘና

    • የመፍሰስ አቅምን እና የውሃ-ሲሚንቶ መጠንን ይለካል
    • ከፍተኛ ስለምፕ = ከመጠን በላይ ውሃ = ደካማ ኮንክሪት
    • ዝቅተኛ ስለምፕ = ደካማ መጠቅጠቅ እና የማር እንጀራ ያስከትላል

    የአርማታ (የኮንክሪት) ጥንካሬ ቅድመ ማረጋገጫ

    • በዋና ዋና የኮንክሪት ሙሊቶች ወቅት የኩብ ናሙናዎች ይውሰዱ
    • በ7 እና በ28 ቀናት ቴስት ማሰራት
    • የዲዛይን ጥንካሬ ላይ መድረሱን ያረጋግጡ

    የተለመዱ ትክክል ያልሆኑ አሰራሮች

    • ኮንክሪቱ በቀላሉ እንዲፈስ ከመጠን በላይ ውሃ መጨመር
    • የናሙና ኩቦችን ወደ ላብራቶሪ ወስደው አለማስመርመር
    • የወደቁ የምርመራ ውጤቶችን ችላ ማለት

    የባለሙያ ምክር

    • የአርማታ (የኮንክሪት) ቡኮውን ቅልቅል ዲዛይኖች ያረጋግጡ
    • የኮንክሪት ምርመራ ውጤቶች መዝገብ ይያዙ
    • ፎርማኖችን ስለምፕ ቴስት እና በኩብ ናሙና መውሰድ ላይ ማሰልጠን

    6. ጡቦች እና ብሎኬቶች — የህንፃዎ ቆዳ

    ለምን አስፈላጊ ሆነ

    ደካማ ብሎኬቶች መጠቀም ግድግዳዎች መሰነጣጠቅ፣ ፕላስተር መውደቅ እና የማያቋርጥ ጥገና ይዳርጋል።

    አስፈላጊ ማረጋገጫዎች

    • የአርማታ (የኮንክሪት) ጥንካሬ ቅድመ ማረጋገጫ
    • ውሃ የመምጠጥ ምርመራ
    • የፍሌርሰንስ ምርመራ

    የተለመዱ ትክክል ያልሆኑ አሰራሮች

    ያለ ማረጋገጫ ዝቅተኛ ጥራት ያላቸውን ብሎኬቶች መጠቀም።

    የባለሙያ ምክር

    በጅምላ ከመግዛትዎ በፊት የተወሰኑ ናሙናዎችን ቴስት ያድርጉ። ቴስቱ ርካሽ ነው። ግድግዳዎችን እንደገና መገንባት ውድ ነው።


    7. የውሃ ስርገት መከላከያ ማረጋገጫዎች — ምክንያቱም ፍሳሾች የእድሜ ልክ ናቸው

    ለምን አስፈላጊ ሆነ

    ህንፃው ካለቀ በኋላ ጥገና ማከናወን ሳያልቅ ከመጠገን በ10 እጥፍ ዋጋ ይጨምራል።

    ማረጋገጥ ያለቦት ቦታዎች

    • የጣሪያ ወለል ውሃ ማቆር ቴስት
    • የመታጠቢያ ቤት እና የበረንዳ የጎርፍ ቴስት
    • የቤዝመንት ፍሳሽ ስርገት

    የተለመዱ ትክክል ያልሆኑ አሰራሮች

    የውሃ መከላከያ ሽፋኖችን ሳያረጋግጡ ማልበስ።

    የባለሙያ ምክር

    የተረጋገጠ የውሃ መከላከያ ውጤት ሳይቀበሉ የሴራሚክ ወይም ፕላስተር ስራ አይጀምሩ።


    8. የኤሌክትሪክ መከላከያ እና ግራውንዲንግ ቴስቶች - ለደህንነቶ ቅድሚያ ይስጡ

    ለምን አስፈላጊ ሆነ

    በትክክል ያልተሰራ የኤሌክትሪክ መስመር ንዝረት፣ እሳት እና የመሳሪያዎች ጉዳት ያስከትላል።

    አስፈላጊ ማረጋገጫዎች

    • የኢንሱሌሽን የመቋቋም ቴስት
    • የግራውንዲንግ ቴስት

    የተለመዱ ትክክል ያልሆኑ አሰራሮች

    "የኤሌክትሪክ ባለሙያው አጠናቋል" ማለት የኤሌክትሪክ መስመር ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ማለት አይደለም።

    የባለሙያ ምክር

    የተረጋገጠ የኤሌክትሪክ ሙከራ ቴስት ሪፖርቶች ሳይኖሩ የኃይል ግንኙነት አለማድረግ።


    9. የቧንቧ ግፊት ቴስት — የተደበቁ ብልሽቶችን መከላከል

    ለምን አስፈላጊ ሆነ

    በግድግዳዎች ውስጥ የሚከሰት ፍሳሽ ማለት መፍረስ፣ ሴራሚክ መንቀል እና ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ጥገና ማለት ነው።

    የምርመራ ዘዴ

    ከፕላስተር ወይም ከሴራሚክ ስራ በፊት የሃይድሮስታቲክ ግፊት ቴስት ማሰራት።

    የተለመዱ ትክክል ያልሆኑ አሰራሮች

    ጊዜ ለመቆጠብ ቴስቱን መዝለል።

    የባለሙያ ምክር

    የተፈረመ የግፊት ሙከራ መዝገብ ከሌለ ምንም ግድግዳ መዘጋት የለበትም።


    10. የመጨረሻ መዋቅራዊ ኦዲት — የመጨረሻው የደህንነት መስመር

    ለምን አስፈላጊ ሆነ

    የመጨረሻ ርክክብ እና ሰነዶች የማንኛውም ፕሮጀክት አስፈላጊ የማጠቃለያ ደረጃዎች ናቸው። በጥገና ወይም በእድሳት ወቅት፣ እነዚህ ዋና አስፈላጊ ሰነዶች ናቸው።

    ከርክክብ በፊት በብቁ መሐንዲስ የሚከተሉትን ማረጋገጥ አለቦት፡

    • የተገነባው ፕሮጀክት ከፀደቁ ንድፎች ጋር እንደሚጣጣም
    • ምንም ያልተፈቀዱ ማሻሻያዎች አለመኖራቸውን
    • የመዋቅር ክብደት እና ጫና የሚተላለፉበት መንገዶች አለመቀየራቸውን
    • የተገባደደውን ግንባታ የሚያሳዩ ንድፎች መዘጋጀታቸውን

    የተለመዱ ትክክል ያልሆኑ አሰራሮች

    ግንባታ ሲጠናቀቅ የረጅም ጊዜ ደህንነት እና ጥገና ተረጋግጧል ብሎ ማሰብ።

    የባለሙያ ምክር

    "ጥሩ ይመስላል" የሚለውን ግምገማ ፈጽሞ አይቀበሉ። ሰነዶችን ይጠይቁ።


    የጥራት ዋጋ ከብልሽት ዋጋ ጋር ሲነጻጸር

    ግንባታ የሚከተለው 1 : 10 : 100 ህግ ነው፡:

    • Spend 1 ብር ዛሬ ለቴስት ቢያወጡ
    • በግንባታ ወቅት ብልሽትን ማስተካከል የሚያወጡት 10 ብር ነው
    • የነዋሪዎች ከገቡ በኋላ ብልሽቶችን ማስተካከል የሚያስወጣው ወጪ 100 ብር ነው — በተጨማሪም ህጋዊ ጉዳት እና የተዓማኒነት ጉድለት ያስከትላል

    ለመደበኛ በአዲስ አበባ ለሚገነባ G+3 ህንፃአስፈላጊ የጥራት ምርመራዎች በጥቅሉ ዋጋቸው ከ100,000 ብር በታች ነው፡ ብዙ ጊዜ የግንባታውን ወይም የፕሮጀክቱን አጠቃላይ ዋጋ 2% አይወስዱም።.

    የማረጋገጫ ምርመራዎችን መተው ገንዘብ መቆጠብ አይደለም።
    አደጋውን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ ነው።


    የመጨረሻ ምክር፡ አንድ ጊዜ በትክክል እንገንባ።

    የጥራት ማረጋገጫ ለትላልቅ ፕሮጀክቶች ቅንጦት አይደለም።
    ይህ ለእያንዳንዱ ሕንፃ አስፈላጊ ነገር ነው - ከመኖሪያ ቤቶች እስከ የንግድ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች።

    ምርጥ የፕሮጀክት ባለቤቶች እና አስተዳዳሪዎች አንድ ልማድ ይጋራሉ፡

    ከማመናቸው በፊት ያረጋግጣሉ።


    የግንባታ ማህበረሰባችንን ይቀላቀሉ

    ለአጠቃቀም ምቹ የሆኑ ሰነዶች፦

    • የግንባታ ጥራት ፍተሻ ዝርዝሮች
    • የኮንክሪት ኩብ የቴስት መዝገብ ቅጾች
    • የውሃ መከላከያ የቴስት ውጤቶች ማስታወሻ
    • የመስክ ላይ ክትትል አብነቶች

    የእኛን የግንባታ ማህበረሰብ እና ሰነዶች ቤተ-መጽሐፍት ይጎብኙ — ለኢትዮጵያ የፕሮጀክት ባለቤቶች፣ አስተዳዳሪዎች እና መሐንዲሶች ተሰናድቶ የቀረበ።