ኮንክሪት የግንባታዎቻችን ዋና ግብዓት ነው - እና ጥንካሬው የሚወሰነው በዲዛይኑ ብቻ ሳይሆን በቦታው ላይ እንዴት መሞላት እንዳለበት ስናውቅ ነው። በጥሩ ሁኔታ የተቀመመ ኮንክሪት እንኳን ሰራተኞች ሙሊቱን በፍጥነት ሲያካሂዱ፣ ውሃ ሳይት ላይ ሲጨምሩ፣ በደንብ ሳይሸከሸክ ሲቀር፣ ወይም መጠጥ ሳይል በማለስለስ ሊበላሽ ይችላል።

ጥሩ የኮንክሪት ሥራ በየቀኑ የሚደረጉ ጥሩ ልምምዶች ናቸው፤ ተገቢ ዝግጅት፣ ትክክለኛ ጊዜ፣ ቋሚ የሥራ ሂደት እና መሰረታዊ የጥራት ምርመራዎች።
1. ከመሙላትዎ በፊት፡ ጥሩ እና ትክክለኛ ዝግጅት ያድርጉ
ውጤታማ የአርማታ (የኮንክሪት) ስራ የመጀመሪያው ቡኬት ጋሪ ከመምጣቱ በፊት ይጀምራል።
የማረጋገጫ ዝርዝር፡

የአርማታ (የኮንክሪት) ቡኮውን ቅልቅል ያረጋግጡ በማስረከቢያ ትኬቱ ላይ - የወ/ሲ (W/C) ምጠና እና የስለምፕ (slump) ከቁጥጥር ሰነዱ ጋር መመሳሰል አለባቸው።

አርማታው (ኮንክሪቱ) የሚደፋበትን ቦታ ያዘጋጁ: የተስተካከለ፣ የተደመደመ፣ እርጥብ - ጭቃማ ወይም ለስላሳ ያልሆነ።

ፎርም ወርክ እና ፌሮዎችን ማጽዳትቆሻሻን፣ የተንጠባጠበ ልስን፣ የዝገት ቅሪቶች ወይም ፍርስራሾችን ያስወግዱ።

የሚሰሩባቸውን መሳሪያዎች ዝግጁ ያድርጉ: ቫይብሬተሮች (ከመጠባበቂያ ጋር)፣ ማለስለሻዎች፣ የግንበኛ ማንኪያዎች።

ትክክለኛውን ሰዐት እና ደቂቃ ይወቁ: አርማታ (ኮንክሪት) ያለምንም መዘግየት ያለማቋረጥ መሞላት አለበት።
2. አርማታ (ኮንክሪት) በሚሞላበት ጊዜ፡- ትላልቅ ስህተቶችን ያስወግዱ
አብዛኛዎቹ የአርማታ (የኮንክሪት) ችግሮች የሚጀምሩት እዚህ ነው - በተለይም ውሃ አጨማመር, መለያየት፣ ወይም ደካማ ሽክሸካ እና ድምደማ.
መደረግ ያለባቸው፡
ኮንክሪት በፍጥነት እና ያለማቋረጥ ይሙሉ።

ተገቢውን ንዝረት (ቫይብሬሽን) በመጠቀም ከአርማታ (ከኮንክሪት) ወስጥ አየር እንዲወጣ በማድረግ የማር እንጀራ እንዳይፈጠር ይረዳል።

መለያየትን ለማስወገድ አርማታ (ኮንክሪት) የሚደፋበትን ቁመት ዝቅተኛ (ከ1.5-2 ሜትር በታች) ያድርጉት።

ማድረግ የሌለቦት ነገር:
በግንባታ ቦታ ላይ ውሃ በጭራሽ አይጨምሩ።

ኮንክሪትን እንደገና አያገላብጡት ወይም ከመጠን በላይ አያዘዋውሩት።

ቀጭን ውፍረት ያላቸውን የግንባታ አካሎች ከመጠን በላይ ንዝረት (ቫይብሬሽን) አይጠቀሙ።

3. ማለስለስ (Finishing)፡ ሰዐት አእና ደቂቃ ወሳኝ ሚና አላቸው
ጥሩ አጨራረስ = ትክክለኛውን ጊዜ መጠበቅ ይጠይቃል።
ወርቃማ ህጎች:

የውሃ ስፈት ባለበት ቦታ ላይ የማለስለስ ስራ አያከናውኑ።

ስራውን የሚጀምሩት አርማታ (ኮንክሪት) የሚያንፀባርቀው ውሃ ከተነነ በኋላ ብቻ ነው።

ማስተካከል → ማሸት → ጠርዝ/መገጣጠሚያ → ማለስለስ።

ለስላሳ ወለሎችን ለመፍጠር፣ አርማታው (ኮንክሪቱ) ጥንካሬውን ካገኘ በኋላ የብረት ማለስለሻ ይጠቀሙ።

ከቤት ውጭ ለሚሰሩ ስራዎች፣ መንሸራተት መለመከላከል የብሩሽ ማለስለሻዎችን ይጠቀሙ።

አየር የገባበትን አርማታ (ኮንክሪት) በጥብቅ አያለስለሱ።
4. ማለስለስ ከጨረሱ በኋላ፡ የአርማታውን (የኮንክሪቱን) ስራ ውጤት የማጠንከር ሂደት ይወስናል
የማጠንከር ሂደት ብዙ ጊዜ በጣም ችላ የሚባለው ደረጃ ነው - ነገር ግን ለጥንካሬ እና ዘላቂነት በጣም አስፈላጊው ደረጃ ነው።
ምርጥ ተሞክሮዎች:
የማለስለስ ስራ እንደጨረሱ ወዲያውኑ የማጠንከር ሂደት ይጀምሩ።

ያለቁ ስራዎችን በትንሹ ለ7 ቀናት እርጥበተቸው መጠበቅ አለበት (ለኦፒሲ አርማታዎች)

ውሃ መርጨት፣ እርጥብ ጆንያ፣ በላስቲክ መጠቅለል ወይም ልዩ ውህዶችን ይጠቀሙ።

አዲስ ያለቁ ቦታዎችን ከፀሐይ፣ ከነፋስ፣ ከዝናብ እና ከትራፊክ እንቅስቃሴ ይጠብቁ።

5. የተለመዱ ችግሮች እና እንዴት ማስተካከል እንደሚቻል
ችግሩ: ማስተካከያው

የማር እንጀራ: የተሻለ እንዲጠቀጠቅ ትክክለኛውን ፈሳሽነት ይጠቀሙ።

የፕላስቲክ መኮማተር ስንጥቆች ከነፋስ/ከፀሐይ፤ ከጭጋግ ወይም ከጥላ ቀደም ብለው ይጠብቁ።

ክሬዚንግ/አቧራማነት፡ ውሃ ባልመጠጠበት ቦታ ላይ ማለስለስ አይስሩ፤ ትክክልኛ የጥንካሬ ሂደቱን ይጠብቁ ያረጋግጡ።

ነጭ ሻጋታ ውሃ ከፎርምወርኮች ውስጥ እንዳይገባ ያድርጉ፤ ፎርምወርኮቹ በደረቅ ሁኔታ እንዲላቀቁ ይጠንቀቁ።

የደረቅ እና እርጥብ አርማታ መገጣጠሚያ: ያለማቋረጥ መሙላትዎን ይቀጥሉ፤ የማይሆን ከሆነ ግን አዲስ ኮንክሪት ከማስቀመጥዎ በፊት ሲሚንቶ የበዛበት ልስን መጀመሪያ ይጠቀሙ።
6. ለአርማታ ሠራተኞች ፈጣን ማስታወሻ
ፕሮጀክቶችን የሚያድኑ ቀላል ህጎች፡
የውሃ-ሲሚንቶ ምጥን (Water–Cement Ratio)
- ቁጥር አንድ ጥንካሬን እና ዘላቂነትን መቆጣጠሪያ መንገድ ነው።
- ዝቅተኛ ው/ሲ (W/C) → ጠንካራ፣ ጥቅጥቅ ያለ፣ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ አርማታ (ኮንክሪት) ይሰጣል።
- አርማታ (ኮንክሪት) በሚሞላበት ቦታ ላይ ውሃ በመጨመር የው/ሲ (W/C) በፍፁም አታስተካክሉ።

የአርማታ ፍሰት (Workability)
- እንደሚሞላው ስራ (ወለል፣ ቢም፣ መሰረት) የፍሰት መጠኑን ይወስኑ።
- ከፍተኛ ፍሰት መጠን ከፍተኛ ጥራት ማለት አይደለም - ብዙውን ጊዜ ከመጠን በላይ ውሃ ተጨምሯል ማለት ነው።

አስፈላጊ የጥራት ምዘናዎች
- የስለምፕ ምዘና
- የሙቀት ልኬት
- የዴንሲቲ ምዘና (እርጥብ አርማታ)
- የጥንካሬ ምዘና በ7፣ 14፣ 28 ቀናት

የአርማታ (የኮንክሪት) ጥንካሬ ቅድመ ማረጋገጫ
- 7 ቀናት፡ ~ ከ60% እስከ 70% የዲዛይን ጥንካሬ
- 14 ቀናት: ~ ከ85% እስከ 90% የዲዛይን ጥንካሬ
- 28 ቀናት፡ የዲዛይን ሙሉ ጥንካሬ

ማጠቃለያ
የአርማታ (የኮንክሪት) ጥራት የሚወሰነው በመስክ ላይ በሚደረገው ክፍተኛ ጥንቃቄ ነው። በትክክለኛ ዝግጅት፣ በተቆጣጠረ አሞላል፣ በትክክለኛ ጊዜ ማጠናቀቅ እና በሥርዓት የማጠንከሪያ ሂደት መከተል፤ የግንባታ ሰራተኞች ጠንካራ፣ ዘላቂ እና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የአርማታ (የኮንክሪት) መዋቅሮችን መስራት ይችላሉ።
ከዚህ በላይ ስላለው ጽሑፍ ምን ያስባሉ?
ከታች ባለው የአስተያየት መስጫ ሳጥን በኩል ሃሳብዎን ያካፍሉ።
ወይም

