መለያ፥ የመጓጓዣ ምህንድስና

  • Exploring Civil Engineering Study Areas: Structural, Geotechnical, Transportation, and More

    የሲቪል ምህንድስና ትምህርት አይነቶችን ማሰስ፡ መዋቅራዊ፣ ጂኦቴክኒክ፣ ትራንስፖርት እና ሌሎችም

    From clean water that we drink everyday; to roads/highway that we travel on; to sweet home house buildings that we dwell, all have the finger prints of civil engineering. Civil engineering as a backbone of civilization through out history. It serves the need of people and communities by designing and building houses, buildings, bridges, railways, tunnels, water treatment plants, pipe lines, and so on.

    civil engineering sub-fields

    ሲቪል ምህንድስና የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ከእቅድ አንስቶ፣ በዲዛይን፣ በግንባታ/ግንባታ፣ ቁጥጥር እና በጥገና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደርጋል። ሲቪል ምህንድስና ቆሻሻን እና ብክለትን ለመቆጣጠር የሚረዱ መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢን እዲኖር ያደርጋል።

    በዚህ ርዕስ ላይ ጠቃሚ መጽሐፍትን ያንብቡ

    የሲቪል ምህንድስና አስደናቂ ገጽታዎች
    በ ኤል ኢ ካርማይክል

    መጽሐፉ የሲቪል መሐንዲሶችን ታሪክ እና ሚና አጉልቶ ያሳያል፣ እንደ ድልድይ፣ ዋሻዎች እና ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ያሉ ታዋቂ ፕሮጀክቶች ያወራል፣ አንባቢዎችን በገሃዱ ዓለም ምሳሌዎች እና የስራ ግንዛቤዎች የሚያስተምር ነው።

    ተጨማሪ መጽሐፍት

    የሲቪል ምህንድስና መስክ አጠቃላይ እይታ
    በ ሼንግ ታኡር ማው

    መፅሃፉ ሙያውን የሚያስተዋውቅ ሲሆን ታሪኩን ፣ ዋና ዋና ቅርንጫፎቹን እና መሐንዲሶች መሰረተ ልማትን በመንደፍ እና በመንከባከብ ረገድ የሚጫወቱትን ወሳኝ ሚና አብራርቷል።

    ሲቪል ምህንድስና፡ በጣም አጭር መግለጫ
    በ ዴቪድ ሙር ውድ

    መጽሐፉ ስለ ሙያው አጭር እይታን ያቀርባል፤ ከታሪኩ ጀምሮ፣ ቁልፍ ሰዎችን እና እንደ ድልድይ፣ ዋሻዎች እና የውሃ ስርዓቶች ያሉ አስፈላጊ ስራዎችን በመዳሰስ የኢነርጂ እና የዘላቂነት ዘመናዊ ተግዳሮቶችን ጭምር ይተነትናል።

    ምህንድስና በግልጽ እይታ - ለተገነባው አካባቢ የመስክ መመሪያ
    በ ግራዲ ሂልሃውስ

    መጽሐፉ ከኤሌክትሪክ መስመሮች እና ድልድዮች፤ እስከ የውሃ ስርዓቶች እና ዋሻዎች፤ በአካባቢያችን ያሉ መሠረተ ልማቶች እንዴት እንደሚሠሩ ያገልጻል። አብዛኛውን ጊዜ ሳይስተዋሉ የሚታለፉ የዕለት ተዕለት የምህንድስና ስራ ውጤቶችን፤ መሐንዲሶች ያልሆኑ ሰዎች የተገነባውን አካባቢ በአዲስ አይኖች “እንዲያዩ” ለመርዳት፣ እንዲያውቁ ለማድረግ በግልጽ ጽሑፍ፣ ስዕላዊ መግለጫዎች እና አጭር ማብራሪያዎችን ተጠቅሟል።

    የከተማ ምህንድስና፡ መሠረተ ልማት እንዴት እንደሚሰራ (ፕሮጀክቶች እና መርሆዎች ለጀማሪዎች)
    በ ማቲስ ሌቪ እና ሪቻርድ ፓንቺክ

    መጽሐፉ እንደ ውኃ፣ ኤሌክትሪክ፣ ጋዝ፣ ፍሳሽ ማስወገጃ፣ ድልድይ፣ መንገድ እና ሽቦ ያሉ የተደበቁ የከተማ ሥርዓቶች እንዴት እንደሚሠሩና አገልግሎት እንደሚሰጡ ያብራራል። እነዚህ መሠረተ ልማቶች በከተማ ዕድገት እንዴት እንደተሻሻሉ ይዳስሳል፤ መርሆችን ለማስተማር ሥዕላዊ መግለጫዎችን፣ ሙከራዎችን እና ጨዋታዎችን ይጠቀማል፤ እና ሁለቱንም የሚታዩ እና የማይታዩ የከተማ ምህንድስና ክፍሎችን ያሳያል

    The Corniche mixed-use development, three landmark towers, London
    የኮርኒሽ ቅይጥ ህንፃ ልማት፣ ሶስቱ ልዩ ማማዎች፣ ለንደን

    መዋቅራዊ ምህንድስና (ስትራክቸራል ምህንድስና)

    መዋቅራዊ ምህንድስና ግንባታውች ላይ የሚያርፉ ወይም የሚመጡ ኃይሎች ካጠና በኋላ እነዚህ ኃይሎች ወደ መሬት እንዴት ያለስጋት እንደሚተላለፉ ይወስናል።

    ለተጨማሪ ማብራሪያ መዋቅራዊ ምህንድስና (ስትራክቸራል ምህንድስና)

    መዋቅራዊ ምህንድስና በአንድ መዋቅር ላይ የሚከሰቱ ኃይሎችን ያጠናል፤ እነዚህ እንዴት መሸከም እና በትክክል ወደ መሬት ማስተላለፍ እንደሚቻል የተለያዩ ስሌቶችን ይሰራል። ኃይሎቹ ከሰው፣ ከእንስሳት፣ ከተሽከርካሪ፣ ከነፋስ፣ ከመሬት መንቀጥቀጥ፣ ከውሃ፣ ወዘተ ሊመጡ ይችላሉ።

    በህንፃ ግንባታዎች ላይ መዋቅራዊ (ስትራክቸራል) መሐንዲስ ከሥነ-ሕንፃ መሐንዲስ ንድፎችን ይቀበላል። ከዚያም ሸክሞችን ለመሸከም እና መሬት ላይ ለመቆም የሚያስችል የሕንፃውን የተለያዩ ክፍሎች (ምሶሶዎች፣ አምዶች፣ ማገሮች፣ ወዘተ) ተንትኖ ይነድፋል። በተጨማሪም መዋቅራዊ (ስትራክቸራል) መሐንዲሶች በድልድዮች፣ ማማዎች እና ሌሎች የሲቪል ምህንድስና መዋቅሮች (ስትራክቸሮች) ላይም በተመሳሳይ ስራዎች ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደርጋሉ። እንደ መዋቅሩ (ስትራክቸሩ) ዓይነት የመዋቅር (ስትራክቸራል) መሐንዲሶችን የሕንፃ፣ የድልድይ፣ ሌላም መዋቅራዊ (ስትራክቸራል) መሐንዲስ ወዘተ ተብለው ይሰየማሉ።

    ጂኦቴክኒካል (የአፈር ምርመራ) ምህንድስና

    ይህ መስክ መሬቱ እንደ ህንፃዎች፣ ድልድዮች እና ግድቦች ያሉ መዋቅሮች በአስተማማኝ ሁኔታ መሸከም እንዲችል የአፈር እና የድንጋይ አለት ጥንካሬ እና ባህሪ ያጠናል።

    Bridge pier supported the ground
    በህንድ ሙምባይ የኬብል ተንጠልጣይ ድልድይ ምሰሶዎች
    ለተጨማሪ ማብራሪያ ጂኦቴክኒካል (የአፈር ምርመራ) ምህንድስና

    ሁሉም በሚባል ደረጃ የሲቪል ምህንድስና መሰረተ ልማቶች በተፈጥሮ እና/ወይም ሰው ሰራሽ መሬት ላይ ይቀመጣሉ/ያርፋሉ። የጂኦቴክኒክ (የአፈር ምርመራ) ምህንድስና የመሬቱን የመሸከም አቅም እና መስጠም ባህሪ ያጠናል። ይህ መስክ በመሬት ውስጥ ያለውን የአፈር እና የድንጋይ ባህሪ እና ጥንካሬ ያጠናል።

    ግዙፍ ግንባታዎች ለምሳሌ፦ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች፣ ድልድዮች፣ ግድቦች፣ ወዘተ ያሉ መዋቅሮች (ስትራክቸሮች) በሚያርፉበት መሬት ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራሉ። ይህ ጫና ወይም ክብደት ግንባታዎቹ ያረፉበት መሬት ውስጥ ውጥረት እና መስጠም ያስከትላል። እነዚህ ውጥረቶች እና የመስጠም አዝማምያዎች ከሚፈቀደው ገደብ በላይ ከሆኑ፤ ህንጻው ወይም ድልድዩ ሊወድቅ ወይም ሊያዘም ይችላል። በተጨማሪም ይህ መስክ ስለመሬት መንሸራተት እና መሬት መንቀጥቀጥ ያጠናል።

    የግንባታ ግብዓቶች (ቁሳቁስ) ምህንድስና

    የግንባታ ግብዓቶች (እቃዎች) ምህንድስና ጥራትን የሚያረጋግጡ መስፈርቶችን በማዘጋጀት፣ በቤተ ሙከራ፣ እና በመስክ ውስጥ የቁሳቁስ ባህሪን በማጥናት ላይ ያተኩራል።

    ለተጨማሪ ማብራሪያ የግንባታ ግብዓቶች (ቁሳቁስ) ምህንድስና

    የግንባታ እቃዎች የሲቪል ምህንድስና መዋቅሮችን (ስትራክቸሮችን) ለመገንባት ወይም ለመስራት የሚያገለግሉ እቃዎች ወይም ነገሮች ተብለው ሊገለጹ ይችላሉ። እንደ ኮንክሪት፣ ድንጋይ፣ እንጨት፣ ብረት፣ አስፋልት፣ አፈር፣ ጡቦች፣ ብሎክይቶች፣ አሉሚኒየም፣ መስታወቶች፣ ፕላስቲኮች፣ ጂኦሲንቲቲክስ፣ ወዘተ የመሳሰሉ ብዙ የግንባታ እቃዎች አሉ። እነዚህ ቁሳቁሶች ሸክሞችን ለመሸከም እና ሌሎች የአካባቢ ሁኔታዎችን ለመቋቋም ልዩ ጥራቶች ሊኖራቸው ይገባል።

    የግንባታ ግብዓቶች (እቃዎች) ምህንድስና የእነዚህን ቁሳቁሶች ባህሪ በመስክ እና በቤተ ሙከራ ላይ ያጠናል። የታቀደውን ጥራት ለመድረስ የተወሰኑ መስፈርቶችን ያበጃል።

    የመጓጓዣ (የትራንስፖርት) እና የትራፊክ ምህንድስና

    የመጓጓዣ (የትራንስፖርት) እና የትራፊክ ምህንድስና ለልማት እና እድገት አስፈላጊ የሆነውን ቀልጣፋ ትራንስፖርት ለማስቻል መሰረተ ልማቶችን ማቀድ፣ መንደፍ፣ መገንባት እና ማስተዳደርን ያካትታል።

    በሞስኮ, ሩሲያ ውስጥ ውስብስብ የሀይዌይ እና የባቡር መስመር ማሳለጫ
    ለተጨማሪ ማብራሪያ የመጓጓዣ (የትራንስፖርት) እና የትራፊክ ምህንድስና

    መጓጓዣ በአጠቃላይ ሰዎችን፣ ሸቀጦችን፣ ቁሳቁሶችን፣ እንስሳትን እና የመሳሰሉትን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ማንቀሳቀስ ወይም መውሰድ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል። ለዚሁ ዓላማ መጓጓዣዎች እንደ ጋሪዎች፣ ተሽከርካሪዎች፣ አውቶቡሶች፣ የጭነት መኪናዎች፣ ባቡሮች፣ አውሮፕላኖች፣ ወዘተ ያስፈልጋል። እነዚህ መጓጓዣዎች የሚጠቀሙበት መንገዶች፣ ድልድዮች፣ የባቡር መስመሮች እና የአየር ማረፊያዎች መሠረተ ልማቶች ያስፈልጋቸዋል።

    የትራንስፖርት እና የትራፊክ ምህንድስና እነዚህን መሠረተ ልማቶች ማቀድ፣ መንደፍ፣ መገንባት/መስራት፣ ማስተዳደር እና መንከባከብ ነው። ማንኛውም ከፍተኛ የእድገት ግብ ያለው ህዝብ ወይም ሀገር ትክክለኛ እና ቀልጣፋ የትራንስፖርት እና የትራፊክ አስተዳደር ስርዓቶችን ሊኖረው ይገባል።

    የግዙፍ ኮንክሪት ስበት (ግራቪቲ) ግድብ፣ ላጋን ዳም፣ ስኮትላንድ ተራራማ አካባቢዎች

    የሃይድሮሊክ ምህንድስና

    የሃይድሮሊክ ምህንድስና ውሃ እንዴት እንደሚንቀሳቀስ እና የእንቅስቃሴውን ባህሪ በማጥናት ላይ ያተኩራል። እና እንደ ግድቦች፣ ቦዮች እና ድልድዮች ያሉ ግንባታዎችን በመንደፍ ውሃ በሚፈለገው ቦታ ለመቆጣጠር፣ ለማከማቸት እና ለማዳረስ ይሰራል።

    ለተጨማሪ ማብራሪያ የሃይድሮሊክ ምህንድስና

    ሁሉም ህይወት ያላቸው ነገሮች ለመኖር ውሃ ይፈልጋሉ። ይሁን እንጂ ውሃ በሁሉም ቦታ አይገኝም። ይህ ማለት ውሃን ከአንድ ቦታ ማጓጓዝ ያስፈልጋል። የሃይድሮሊክ ምህንድስና በመንፈልገው አካባቢ ውስጥ የውሃ እንቅስቃሴን እና ማጠራቀምን ያጠናል።

    የሃይድሮሊክ ኢንጂነሪንግ የውሃ እንቅስቃሴን እንደ ፈሳሽ ኃይል እና ውጤት ይተነትናል። ሃይድሮሊክ ኢንጂነሪንግ ለግድቦች፣ ድልድዮች፣ የመስኖ ቦዮች፣ ድልድዮች ወዘተ ሞዴሎችን በማዘጋጀት ውሃ ተከማችቶ ወደታሰበበት ቦታ ያለ ምንም ችግር እንዲጓጓዝ ያደርጋል።

    የአካባቢ ምህንድስና

    የአካባቢ ምህንድስና የአካባቢን እና የህዝብ ጤናን ልመጠበቅ ይሰራል፤ ውሃን፣ አየርን እና ቆሻሻን ለመቆጣጠር እና ለማስወገድ የሚረዱ ግንባታዎች በመንደፍ፣ በመገንባት እና በማስተዳደር ነው። በዚህ መስክ ውስጥ ያሉ ሲቪል መሐንዲሶች እንደ ንፁህ ውሃ አቅርቦት ፣ የቆሻሻ ውሃ ማጣሪያ ፣ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓቶች ፣ የብክለት ቁጥጥር እና ዘላቂ የግንባታ ልምዶች ባሉ ፕሮጀክቶች ላይ ይሰራሉ።

    ለተጨማሪ ማብራሪያ የአከባቢ ምህንድስና

    ይህ የሲቪል ምህንድስና መስክ የአካባቢን ሀብቶች አጠቃቀም ከሚያጠናው የአካባቢ ሳይንስ ጋር የተዋሀደ ነው። የአካባቢ ምህንድስና ጥናቶችን፣ እቅዶችን፣ ንድፎችን፣ መስሪያ ቦታዎችን ለሚከተሉት ዓላማዎች ይገነባሉ፦

    • ለሰዎች ንጹህ ውሃ ለማቅረብ
    • የቆሻሻ ውሃ አያያዝ
    • የብክለት ቁጥጥር
    • ቆሻሻ መሰብሰብ እና ማስወገድ

    በአጠቃላይ የአካባቢ ምህንድስና ንፁህ የመጠጥ ውሃ እና የምንኖርበት አካባቢ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን የማከሚያ ፋብሪካዎችን በመገንባትና ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዎችን በማዘጋጀት አስተዋጽኦ ያደርጋል።

    የግንባታ አስተዳደር

    የኮንስትራክሽን አስተዳደር ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ፣ በበጀት እና በጥራት እና በደህንነት ደረጃዎች መጠናቀቁን ያረጋግጣል። የግንባታ ፕሮጀክትን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የማቀድ፣ የማስተባበር እና የመቆጣጠር ሂደትን ያካትታል።

    ለተጨማሪ ማብራሪያ ግንባታ አስተዳደር

    ከላይ የተገለጹት አብዛኛዎቹ የሲቪል ምህንድስና መስኮች እርስ በርስ የተያያዙ ሲሆኑ የተወሰኑ መዋቅሮችን (ስትራክቸሮችን) ማቀድ፣ መተንተን፣ መንደፍ እና ሞዴል ማድረግን ያካትታሉ። እነዚህን መዋቅሮች (ስትራክቸሮች) በትክክል ለመገንባት ወይም ለመስራት የግንባታ አስተዳደር ያስፈልጋል። የኮንስትራክሽን አስተዳደር ዕቅዶች፣ ግምቶች፣ ጨረታዎች፣ ግንባታዎች እና ሁሉንም የሲቪል ምህንድስና መዋቅሮችን (ስትራክቸሮችን) መጠገን ያካትታል።

    የግንባታ አስተዳደር የሚጀምረው የአንድን ፕሮጀክት ፍላጎትና መስፈርቶች በማጥናት ነው።

    ክለሳ

    ሲቪል ምህንድስና የዕለት ተዕለት ህይወታችን ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀላል የሚያደርጉ ልዩ ልዩ መዋቅሮችን የሚገነባበት እና/ወይም የሚሰራበት የኑሯችን ወሳኝ አካል ነው። ሲቪል ምህንድስና የሚከተሉትን ያቀርባል፦

    • አስተማማኝ እና ምቹ ቤቶች፣ ሕንፃዎች፣ ቢሮዎች
    • ፈጣን እና ምቹ መንገዶች ፣ ድልድዮች ፣ የባቡር መስመሮች ፣ የአየር ማረፊያዎች
    • የመጠጥ፣ የመታጠቢያ፣ የመዋኛ ውሃ
    • ለጤናማ አካባቢ የቆሻሻ ውሃ አያያዝ
    • የብክለት ቁጥጥር እና ቆሻሻ አያያዝ
    • የተፈጥሮ አደጋዎች ለመቀነስ የሚረዱ መመሪያዎች

    ከላይ ያለውን የአኗኗር ዘይቤ ለመጠበቅ የሲቪል ምህንድስናን በትክክል ማጥናት እና መተግበር አስፈላጊ ነው። ፕሮጄክቶችን ለማካሄድ በእያንዳንዱ ልዩ መስክ ውስጥ ያሉ የሲቪል ምህንድስና ባለሙያዎች መቅጠር እና መጠቀም አስፈላጊ ነው። በሚቀጥለው ጽሑፋችን ከሲቪል ምህንድስና ጋር በተያያዘ የተከሰቱ አደጋዎች እና መንስኤዎቻቸውን እንተነትናለን።

    ከታች ባለው የአስተያየት መስጫ ሳጥን በኩል ሃሳብዎን ያካፍሉ።

    ወይም